TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ልኡክ ጄፈሪ ፊልትማን ጋር መወያየታቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ይፋ ባደረገው መረጃ ፤ በውይይቱ ወቅት ከአሸባሪው ሕወሐት ጋር የሚደረገው ጦርነት ስለሚቆምበት መንገድ የአሜሪካ ሐሳብ ምን እንደሆነ በልዩ ልኡኩ በኩል የተነሣ ሲሆን፣ አቶ ደመቀ የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን #በኮምቦልቻ እና #በላሊበላ ለሰብአዊ ርዳታ የሚውሉ በረራዎች መፈቀዳቸውን የገለፁ ሲሆን ወደ ትግራይም 369 ርዳታ የጫኑ መኪናዎች እንዲገቡ መፈቀዱን ገልፀዋል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎችን ሁኔታ በተመለከተም ውይይት አድርገዋል።

አቶ ደመቀ ፥ " አሸባሪው ሕወሐት አሁንም ቢሆን በአፋርና በአማራ ክልሎች ጥቃት እየፈጸመና ከፍተኛ ሰብአዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት እንዲሁም ሥነ ልቡናዊ ጉዳት እያደረሰ ነው " ያሉ ሲሆን ህወሓት ከሁለቱ ክልሎች ለቅቆ እንዲወጣ ግፊት ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
👍1