TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.3K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሹመት⬇️

ኢንጂነር ሞገስ ጥበበ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። ኢንጂነር ሞገስ በኮንሰትራክሸን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮንትራት አስተዳደር እና በምህንድስና ግዢ ላይ በሃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ኢንጅነር ሞገስ በቅርቡ የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን እና የቀድሞ የተቋሙን ሃላፊ ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝን ነው የተኩት።

አዲሱ ተሿሚ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን #በአጭር ግዜ ማጠናቀቅ እና የከተማዋን የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ለመፍታት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን መቅረጽ በቀዳሚነት የሚያከናውኗቸውን ተግባራት መሆናቸውንም ተናግረዋል።

©Lebu Area EPRDF Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት ችግር #በአጭር_ቀን ውስጥ #እንደሚፈታ ለመስማት ተችሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በዋናው ዳታ ቤዝ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት ለጊዜው ማቆሙን ገልጿል።

ደንበኞች የተቋረጠው አገልግሎት #በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈቶ ወደ ቀደመ አገልግሎቱ እንስኪመለስ በትእግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ኤጀንሲው ካጋጠመው የሰርቨር ችግር ውጪ በድረ-ገጽ አማካኝነት የሚሰጠው የፓስፖርት አገልግሎት አልተቋረጠም ብሏል።

በኤጀንሲው ዋና ሰርቨር ላይ ያጋጠመው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ በመግባት ቀጠሮ ማያዝ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ያጋጠመውን ችግር ዛሬ ወይንም ነገ አልያም በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እተየሰራ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia