TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመጨረሻ_ቀን

ከብር 100 ሺህ እስከ ብር 1.5 ሚሊዮን ነባሮቹ የብር ኖቶች የመቀየሪያው ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ከዛሬ ጥቅምት 6 በኃላ ከ100 ሺህ ብር እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር ይዞ ወደ ባንክ የሚሄድ ተጠቃሚ በባንኮች አገልግሎት ማግኘት አይችልም ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዓለም አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር ለሩብ ፍጻሜ የደረሰው ኢትዮጵያዊው ወጣት !

አቤል ዳኜ የሠራው በሁካታ መሃል ሆኖ ድምፅን ማጥፋት የሚቻልበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፅንሰ ሃሳብ የሚያስረዳው ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገው አቤል ዳኜ የ18 ዓመት ወጣት ሲሆን " ብሬክስሩ፣ ጁኒየር ቻሌንጅ " በተሰኘ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ሂሳብ ውድድር ላይ ከ2400 ሰዎች መካከል ለዕሩብ ፍጻሜ ከደረሱ 30 ሰዎች አንዱ መሆን ችሏል። 

#ቪኦኤ በሰጠው ቃል " ኮምፒውተር ሳይንስ ፍቅሬን ያዳበርኩት ከአባቴ ነው "  የሚለው አቤል የወደፊት ፍላጎቱም ትምህርቱን ጨርሶ #ኢትዮጵያን መርዳት እንደሆነ ተናግሯል።

ባለፈው ክረምትም በደብረ ማርቆስ ሀዲስ ዓለማየሁ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚማሩ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ዌብ ግንባታ ሲያስተምር ቆይቷል። 

አቤል ይህን " ብሬክስሩ " የተሰኘ ሽልማት ካሸነፈ የ250 ሺ ዶላር የነጻ የትምህርት ዕድል፣ 100 ሺ ዶላር ለተማረበት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ቤተ-ሙከራ ግንባታ እና እሱን ላበረታታ እና ላነቃቃ መምህር የ50 ሺ ዶላር ሽልማት የሚያገኝ ይሆናል።

ነገር ግን ይሄ ይሆን ዘንድ " ብሬክስሩ ቻሌንጅ " የፌስቡክ እና የዩቱብ ገጽ ላይ ሰዎች ላይክ፣ ኮሜንት በማድረግ እንዲያግዙት ጠይቋል።

የህዝብ ድምፅ አሰጣጡ #የመጨረሻ_ቀን ዛሬ መስከረም 10 (September 20) ነው። #አሁኑኑ በፍጥነት የሚከተሉትን 2 ቪድዮዎች  ‘Like’ አድርጋችሁ ድምፃችሁን ስጡት።

1. Facebook https://www.facebook.com/watch/?v=595860615362156
2. YouTube https://www.youtube.com/watch?v=PzTAhCHoIMQ&feature=youtu.be

@tikvahethiopia
👍2.1K214🙏62🕊55🥰27😢17👎10😱9