TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዓረና‼️

በሀገር-ዓቀፍ ደረጃ የተጀመረው #ሪፎርም ወደ ክልሎችም በበቂ ደረጃ እንዲወርድ ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ ሉዓላዊነት ፓርቲ ገለፀ፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ሃይልና በአየር የታገዘ የፖሊስ ቡድን እሰከማቋቋም የደረሰ የአደረጃጀት ማስተካከያ አደረገ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል #እንዳሸው_ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ የኮሚሸኑ ተቋማዊ ሪፎርም ሂደት እና የደረሰበትን ደረጃ አብራርተዋል።

የሰው ሃይል፣ ቴክኖለጂ፣ ስልጠና፣ ሎጅስቲክስ እና ከባለደርሻ አካላት ጋር የሚኖር ግንኙነት ላይ መሰረት ያደረገው #ሪፎርም በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በረፎርሙ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አሰፋፈር እና አደረጃጀት #መከለሱን እንዲሁም በአራት አቅጣጫ በአራት ክላስትሮች እንዲከፋፈል መደረጉን ነው የገለፁት። ክላስተሮቹም፥ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምእራብ እና ማእከላዊ ክላስተር ናቸው።

በሪፎርሙ መሰረት የከተማ ልዩ የፌደራል ፖሊስ ሃይል እና #በአየር የታገዘ ክትትል ለማድረግም የፌራል ፖሊስ የአየር ሃይል ክንፍ ( AIR WING ) #ይደራጃልም ብለዋል ኮምሽነር ጀነራሉ።

የጦር መሳሪያ ትጥቅን በተመለከተም የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ እና ልዩ ሃይል እንዲሁም ሚሊሻዎች ምን አይነት መሳሪያ ሊታጠቁ ይገባል የሚለውን የሚመልስ አዋጅ በመዘጋጀት ላይ ነው።

የሪፎርሙ አካል የሆነ የምርመራ ስርኣትን በሚመለከትም የምርመራ ማንዋል ተዘጋጅቶ በቅርቡ ወደ ትግባራ እንደሚገባ ተነግሯል።

#ፌዴራል_ፖሊስ ካሁን ቀደም ከምርመራ ጋር የተያያዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቀረት ካሜራ የተገጠመላቸው፣ በመስታውት የተከለሉ፣ ሶስተኛ ወገን ምርመራውን መከታተል የሚችልባቸው የምርመራ ክፍሎች መዘጋጀታቸውም በመግለጫው ተነስቷል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት‼️

የኢፌድሪ መከላከያ ሚነስቴር እያካሄደ ያለው #ሪፎርም በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ የተጀመረውን ሪፎርም ለማስቀጠልና በታሰበለት መልኩ ለማሳካት የሚያስችል ስልጠናም እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናው ሰራዊቱ ሪፎርሙን እውን በማድረግና የሪፎርሙን የአሰራር ስርዓት በማስቀጠል ወደፊት ለሚኖረው የግዳጅ አፈፃፃም ተልዕኮ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ የወታደራዊ አመራሩን አቅምን ለማሳደግ የታለመው ይኸው ስልጠና በሁሉም የሰራዊቱ ክፍሎች በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከታክቲካል እስከ ኦፕሬሽናል አመራር እርከን ያሉ የሰራዊት አባላትን ያጠቃለለ ነው፡፡ በተጨማሪም ስልጠናው ሰራዊቱ ለህዝቡና ለህገ መንገስቱ ያለውን ታማኝነት በፅናት የሚያረጋግጥበትን አቅም ከፍ የሚያደርግና የሪፎርሙን ግቦች በማሳካት በኩልም ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ ለስምንት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ስልጠናም የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia