TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UNDP

ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን የተመድ የልማት ፕሮግራም (UNDP) የአፍሪካ ዋና የፈጠራ ስራ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

ዶክተር እሌኒ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅትን (ኢ.ሲ.ኤክስ) እንዲሁም ብሉ ሙን የተሰኙ ተቋማትን በመመስረት እና በመምራት ይታወቃሉ።

ዶ/ር እሌኒ የUNDP የአፍሪካ ዋና የፈጠራ ስራ ኃላፊ ሆነው መሾናቸውን ተከትሎ ወደ ኒውዮርክ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአፍሪካ ውስጥ የወጣቶች የፋይናንስ ፈጠራ አብዮት ቲምቡኮትን በማስጀመር ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወቱ UNDP በድረ ገጹ አስነብቧል።

የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ ዲጂታላይዜሽንን ማሳደግ እና ወጣቶችን ማበረታታት ትኩረት አደርገው ይሰራሉ ብዩ አምናለሁ ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ረዳት ዋና ጸሐፊ እና የUNDP የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁንና ኢዚያኮንዋ ገልጸዋል፡፡

#ENA

@tikvahethiopia
👍2