TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እገዳው_ተነስቷል !

ለትንሳኤ በዓል ወደ እስራኤል በሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ላይ ተጥሎ የነበረው የቡድን ጉዞ እገዳ መነሳቱ ተገልጿል።

የእስራኤል የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቡድን ቪዛ እገዳ ጥሎ ነበር።

ሚኒስቴሩ ውሳኔውን አሳልፎ የነበረው በኢትዮጵያ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ተጓዦች ወደ እስራኤል ከመጡ አይመለሱም በሚል ስጋት ነበር።

በተላለፈው ውሳኔው ላይ ቅሬታ የተሰማቸው የተለያዩ አካላት በተለይ በእየሩሳሌም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ገዳም አባቶች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት፣ በእስራኤል የኢፌዴሪ ኤምባሲ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ከሕዝብና ኢሚግሬሽን ጉዳይ የሥራ ኃላፊዎች እና ከሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከተለያዩ አካላት ጋር በተደረገው ተደጋጋሚ ምክክር ውሳኔው የሁለቱን አገራት ወዳጅነት አንጻር ተገቢ አለመሆኑን አሳውቋል።

በመቀጠልም ፤ የእስራኤል የፓርላማ አባል የሆኑት ጋዲ ይባርከን ጋር በመሆን ከእስራኤል ከሕዝብና ኢሚግሬሽን ባለስልጣን ኃላፊዎች ጋር በተደረገው ውይይት ተጥሎ የነበረው የጉዞ ገደብ የተነሳ መሆኑን በእስራኤል ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
👍79976👎60👏24🥰19😱15😢3