TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መልዕክት

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት

- በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲኬድ የፀጥታ አካላት በየቦታው ፍተሻ ያደርጋሉ፤ ይህንንም ህዝበ ክርስትያኑ እንዲገነዘብ ተብሏል። ምናልባት ፍተሻው 2 እና 3 ቦታ ቢሆን እንኳን ፍተሻው ለራስ ደህንነት መሆኑን በመገንዘብ ህዝበ ክርስትያኑ ሳይሰላች ለፍተሻው እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

- ከባንዲራ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ - ወደበዓሉ ቦታ በሚኬድበት ጊዜ ፣ የወጣት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት እንዲሁም ሌሎች አካላት በሀገሪቱ ህገመንግስት የፀደቀውን የፌዴራል አርማ ያለበትን ባንዲራ ብቻ መጠቀም ይገባል ተብሏል፤ አላስፈላጊ ሎጎዎችን እና ህጋዊ ከሆነው ባንዲራ ውጪ መጠቀም አይቻልም፤ ለዚህም ለፀጥታ አካላት ትብብር ማድረግ ያስፈልጋል።

- ከኢትዮጵያ ብሄራዊው ባንዲራ ውጪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት «ነዋ ወንጌለ መንግሥት» የሚል አርማ ያለበትን ባንዲራ መጠቀም ይቻላል፤ ህዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ባንዲራ ሲጠቀም በስነስርስአቱ የታተመ፣ በሁለቱም በኩል ሎጎው እንዳለ የሚያሳይ መሆን አለበት።

- ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲሄድ የኮቪድ-19 መከላከያ ጥንቃቄዎችን መፈፀም እንዳለበት አደራ ተብሏል። ማስክ ያድርጉ፣ ሳኒታይዘር ያዙ ፤ ርቀታችሁንም ጠብቁ።

- የጤና ሚኒስቴር በመስቀል አደባባይ የኮቪድ-19 የክትባት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፤ በቦታው ላይ ክትባት ስለሚሰጥ ቀደም ብሎ በመገኘት የክትባቱ ስነሥርዓት ተሳታፊ መሆን እንደሚቻል ተገልጿል።

- ከመስቀል አደባባይ ውጭ የሚደረጉ የመስቀል ደመራ ስነስርዓቶች የፀጥታ ኃይሎችን በመተባበር እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

- ለበዓሉ ድምቀት በሚል ርችት መተኮስ አይፈቀድም።

@tikvahethiopia
👍41
#መልዕክት

ከሰዓታት በኃላ 2ኛው " የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ " መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ለታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር 2 ለመታደም ሲመጡ ፦

👉 የራሳችሁን መስገጃ ይዛችሁ ኑ።

👉 አዘጋጆች የሚዘጋጁት ምግብ ቢኖርም ሁሉም የቻለውን ያህል ለሰዎች ጭምር የሚሆን ምግብ ይዞ ይምጣ።

👉 ሁሉም የተመገበበትን እቃ የሚያነሳበትን ፌስታል መያዝ እንዳይዘነጋ።

👉 በመሃል ሌባ ሊኖር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።

👉 አቅመ ዳካማዎችን፣ታላላቆችንና ሴቶች የተሻለ ቦታ እንዲያገኙ አድርጉ።

👉 ለአስተናጋጆች፣ ለኻዲሞችና ለፀጥታ አካላት ፍፁም ታዛዥ ይሁኑ።

👉 በጦርነትና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ ለሚንቀሳቀሱ አስተባባሪዎች ድጋፍ ያድርጉ።

👉 እርስ በእርስ በመከባበር እና በመተዛዘን እጅግ የሰለጠነና ምስኪኖችን ታሳቢ ያደረገ ኢፍጣር እንዲሆን ሁላችንም ባለቤቶች እንደሆንን በማሰብ ተግባራዊ ያድርጉ።

📞 ማንኛውም አይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በቦታው ለሚገኙ የፀጥታ አካላትና አስተባባሪዎች ወይም በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111110111 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት ይተባበሩ።

(ከአዘጋጆች)

መልካም የኢፍጣር ስነስርዓት !

#ሼር #Share

@tikvahethiopia