TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 674 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 26,771 ደርሷል።

- የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮና ቫይረስ ከዳኑ በኋላ የመጀመሪያቸውን የሚኒስትሮች ስብሰባ የመሩ ሲሆን ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል፤ አገራቸው የወረርሽኙን ጣሪያ ማለፏን ተናግረዋል - #BBC

- ደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች፤ አራቱም #ከውጭ የገቡ ናቸው።

- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 4 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን አራቱም (4) ከውጭ ከገቡ ናቸው።

- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው ቀንሷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ289 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ62,000 በላይ ሆኗል።

- በአሜሪካ የሥራ አጦች ቁጥር 30 ሚሊየን መድረሱን የአሜሪካ የሰራተኞች መስሪያ ቤት ያወጣው አዲስ መረጃ አሳይቷል - #BBC

- በደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 10,403 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 297 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 5,647 ደርሷል።

- በግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት 12 ሰዎች ሲሞቱ፣ 269 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 5,537 ደርሷል። ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,381 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia