TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና! የደቡብ ሱዳኑ የአማፂ ቡድን መሪ #ሪክ_ማቻር  የሀገሪቱን ሰላም  ለመመለስ የሚያስችለውን የተሻሻለውን ስምምነት #ለመፈረም ፍቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

📌የአማፂ ቡድን መሪው ሀገሪቱ ሊኖራት በሚገባው የክልል #መጠንና #የደንበር ጉዳይ በነበራቸው ቅሬታ ማሻሻያ የተደረገበትን ሁለተኛ ስምምነት ለመፈረም ፍላጎት አልነበራቸውም።

▪️ሆኖም #ከሱዳን መንግስት ጋር በተደረገ ከፍተኛ #ድርድር ሪክ ማቻር የመጨረሻውን የሰላም ስምምነት ለመፈረም መዘጋጀታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አል ዲርዲር መሀመድ ተናግረዋል።

©CGTN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለተገኙት 2 ግለሰቦች!

በጤና ሚኒስቴር እንደተገለፀው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት (2) ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው በክልሉ ግንቦት 5/2012 ዓ.ም ከተላኩት 63 ናሙናዎች መካከል ነው።

ሁለቱ (2) ግለሰቦች የ35 እና የ29 አመት ዕድሜ ያላቸው እና #ከሱዳን በጉባ ወረዳ በአልመሀል ቀበሌ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡና በፖዌ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የቆዩ ናቸው።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ በመገኘቱ ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በጤና ባለሙያዎች የተቀመጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ራሱንና ህብረተሰቡን መታደግ እንዳለበት አሳስብዋል።

(የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrHagosGodefay

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል (ማይ ካድራና ሰቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ) ኮቪድ-19 ስለተገኘባቸው ግለሰቦች የሰጡን አጭር መረጃ ፦

- ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች የ20፣ 26 እና 55 ዓመት እድሜ ያላቸው ናቸው።

- ሶስቱም (3) የመጡት #ከሱዳን ነው።

- አንደኛው ታማሚ ሚያዚያ 29፣ ሁለተኛው ታማሚ ሚያዚያ 30 ፣ ሶስተኛው ደግሞ በግንቦት 1/2012 ዓ/ም ነው ወደ ትግራይ የገቡት።

- ሶስቱም ግለሰቦች ምንም አይነት ምልክት የለባቸውም።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia