" ከሩስያ ጋር በዩክሬን አንዋጋም " - አሜሪካ
የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ #ዩክሬን ውስጥ ከሩስያ ጋር ወደ ውጊያ እንደማይገቡ ተናግረዋል።
ባይደን " ፑቲን ጠብ አጫሪ አጥቂ ናቸው ፤ ይህንን ጦርነት መርጠዋል። እሳቸው እና አገራቸው ውጤቱን ይሸከማሉ " ብለዋል።
በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን ባይደን አሳውቀዋል።
ጆ ባይደን ፥ " የእኛ ሃይሎች በዩክሬን ውስጥ ከሩሲያ ጋር ግጭት ውስጥ አይደሉም እንዲሁም አይገቡም " ያሉ ሲሆን " ሃይሎቻችን በዩክሬን አይዋጉም የኔቶ አጋሮቻችንን እና የኔቶ ግዛትን እያንዳንዱን ኢንች ግን እንከላከላለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ተጨማሪ 7ሺ የአሜሪካ ወታደሮች ወደጀርመን እንደሚያመሩ አሳውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን " ሩሲያ በኩባንያዎቻችን ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ጥቃቶችን የምትቀጥል ከሆነ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነን " ሲሉ ዝተዋል።
@tikvahethiopia

👎1.05K👍605👏53😢52😱37❤20🥰19
#ስንዴ
በ #ዩክሬን እና በ #ሩስያ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በተለይ ከመካከለኛው ምስራቅ ብዙ ማይሎች ርቆ ነው። ነገር ግን ጦርነቱ በርካታ ሰዎችን ችግር ላይ ሊጥል ይችላል ተብሎ ተፈርቷል።
🌾 ሩሲያ እና ዩክሬን በድምሩ 29 በመቶውን የአለም ስንዴ ወደ ውጭ ይልካሉ። ሀገራቱ አሁን ከገቡበት ጦርነት ጋር ተያይዞ በ13 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የስንዴ ዋጋ ንሯል።
ይህ ጦርነት በዚህ ከቀጠለ በርካታ ሀገራት አስከፊ የሆነ ችግር የሚገጥማቸው ሲሆን በተለይም 3 ሀገራት ለከፍተኛ ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ ፤ እነዚህ 3 ሀገራት እነማን ናቸው ?
🇾🇪 የመን
🌾 በጦርነት የደቀቀችው ሀገር የመን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የምግብ ምርቶች ላይ ጥገኛ ናት ፤ ሀገሪቱ ቢያንስ 27 በመቶውን ስንዴ ከዩክሬን እና 8 በመቶውን ከሩሲያ በመግዛት ላይ ነው የምትገኘው።
🥖 በየመን ለ7 አመታት የዘለቀው ግጭት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ህዝቦቿን ለረሃብ ዳርጓል፤ አሁን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ችግሩን በአስከፊ ሁኔታ እያባባሰ ነው።
🇪🇬 ግብፅ
🌾 90 % የሚሆነው የግብፅ ስንዴ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ነው የሚገባው። ግጭቱ አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እያደረሰ ነው።
🌻 ሩሲያ እና ዩክሬን በግብፅ የሱፍ አበባ ዘይት ዋነኛዎቹ አቅራቢዎች ናቸው።
👨🍳 የዳቦ ጋጋሪዎች ከወዲሁ የዱቄት እና የምግብ ዘይት ዋጋ በጣም ውድ ሆነብን እያሉ ነው።
📈 አንድ ዳቦ ጋጋሪ በዱቄት ዋጋ ከ50% በላይ ጭማሪ እና የምግብ ዘይት ዋጋ ላይ አነስተኛ ጭማሪ በመታየቱ ንግዱ ተጎድቷል ብሏል።
🇱🇧 ሊባኖስ
🌾 ሊባኖስ ከዩክሬን 60 በመቶ የሚሆነውን የስንዴ ምርት ታስገባለች።
ሊባኖስ የዩክሬን የሩስያ ጦርነትን ተከትሎ አማራጭ የስንዴ አቅርቦትን እንደምትመለከት ገልፃለች።
🇷🇺 የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ሩሲያ ላይ እንደጉድ እየወረደ ባለው #ማዕቀብ የተነሳ ሩሲያውያን ላይ የከፋ ተፅእኖ ይዞ እየመጣ ነው። ዩክሬንም የጦር ሜዳ በመሆኗ ዜጎቿ ሀገር ጥለው እየተሰደዱ ነው።
ነገር ግን ቀውሱ ከሩሲያ እና ዩክሬን ባለፈ #የስንዴ_ዋጋን እንዲጨምር በማድረግ በመካከለኛው ምስራቅም ምግብ በጣም ውድ እንዲሆን እያደረገው ይገኛል።

👍667😢120😱21👏19👎12🥰7❤6
TIKVAH-ETHIOPIA
ነዳጅ📈 ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በ10 % ወደ ' 107 ዶላር ' ከፍ ብሏል፤ ይህም እኤአ ከ2014 በኃላ ከፍተኛው እንደሆነ ነው የተነገረው። ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ የምትገኘው ሩሲያ በዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ የነዳጅ ዘይት አምራችና ሁለተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ ሀገር ነች። አጠቃላይ ሩሲያ በዓለም የነዳጅ ምርት 10 % ድርሻ አላት። የዩክሬን እና የሩስያ ጦርነት፤ ጦርነቱን…
ነዳጅ📈
ዛሬ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል #ከ110_ዶላር በላይ መድረሱን AFP ዘግቧል።
በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት የ1 በርሚል ነዳጅ ዋጋ በ5.06 በመቶ ጨምሮ 108.64 ዶላር ደርሷል።
ሁለቱም ላይ እንደእኤአ ከ2014 በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛው ጭማሪ መሆኑ ተነግሯል።
የቀጠለው የ #ሩስያ እና #ዩክሬን ጦርነት መላው ዓለም ላይ ተፅእኖው በየዕለቱ እያየለ ነው።

👍414😱113😢70👎40❤24👏9🥰8