TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዋግኽምራ📍

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ህወሓት በሚቆጣጠረው አበርጌሌ በተፈጠረው የመድሃኒትና ምግብ እጥረት ሳቢያ ከሃምሌ ወር አንስቶ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱ ተገልጿል።

ወረዳው ከሟቾቹ ውስጥ ብዛት ያላቸው ህፃናት እና አዛውንት እንደሆኑ፤ አብዛኞቹ ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነበረባቸው ነገር ግን የሞታቸው ምክንያት የመድሃኒት እጥረት መሆኑ አሳውቋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አለሙ ክፍሌ ሲናገሩ፥ "ከ70 ሺ ህዝብ በላይ ነው አበርጌሌ የሚኖረው፤ አበርጌሌ ማለት ከትግራይ በሜትር ልዩነት የምንኖር ማህበረሰቦች ነን።

እዛ ያለው ማህበረሰብ አሁን በረሃብ እየሞተ ነው ያለው። ከ120 በላይ ሰው በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ሞቷል።

በአብዛኛው የሞቱት ሽማግሌዎች የነበሩ እና ከ50 በላይ እድሜ ያላቸው መንቀሳቀስ የማይችሉ በረሃብ እና በእድሜም ትንሽ ከፍ ያሉ ናቸው አንዳንዶቹ የግፊት መድሃኒት ይጠቀሙ የነበሩ ናቸው። አንዳንዶቹ የኤች አይቪ መድሃኒት የሚጠቀሙ ነበሩ።

ከዛ በዘለለ የተጠቁብን ህፃናቶች ናቸው በወባ እና በተለያዩ በሽታዎች ህክምና እና መድሃኒት የሚባል ስለሌለ ህፃናቶች ናቸው የሞቱት " ብለዋል።

አካባቢው በህወሓት ቁጥጥር ስር ከዋለ እንዴት የሟቾች ቁጥር ተረጋገጠ ? ለሚለውም ሲመልሱ፦

" አንደኛ ቤተሰቦቻችን ናቸው፣ አብዝሃኛው በየቀበሌው ያሉ ሰዎችም እዚህ ስለሚመጡ በተፈናቃይ መልኩ መረጃ ይሰጡናል።

በየቀኑም መረጃ የሚሰጡን ሰዎች አሉ እዛ ሆነው። በየቀኑ ምን እንደተፈጠረ ምን እንደሆነ ዝርዝር መረጃ የሚሰጡን አሉ።

እዛው አበርጌሌ ውስጥ አንዳንድ ቀበሌዎች ኔትዎርክ የሚሰራባቸው አሉ፤ ስልክ ስለሚሰራ በየቀኑ መረጃ እናገኛለን ይሄን በጣም እርግጠኛ ነኝ። " ሲሉ መልሰዋል።

telegra.ph/VOA-04-06

@tikvahethiopia
👍329😢246👎23😱139👏8
#ዋግኽምራ📍

ጦርነት ክፉኛ ከጎዳቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች አንዱ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ነው።

በእዚህ አካባቢ ያሉ ወገኖች ለከፋ ችግር ተጋልጠው ሜዳ ላይ መውደቃቸው እና አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጥሪ ሲቀርብ እንደነበር ይታወሳል።

ምንም እንኳን በቂ ባይሆንም የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ ተስተውሏል።

ዛሬ ከዋግ ኽምራ ኮሚኒኬሽን በተገኘ መረጃ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው በሰቆጣ መጠለያ ለሚገኙ የዋግ ተፈናቃዮች 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስንዴ (300 ኩንታል) ድጋፍ አድርጓል።

ዩኒቨርሲቲው በችግር ላይ ለወደቁት ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳውቋል።

በተጨማሪ በዞኑ የተለያዩ ምርምሮችን ተግባራዊ በማድረግ የህብረትሰቡን ችግር ለመፍታት የበኩሉን እንደሚወጣ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahethiopia
👍335😢35👎2011👏5🥰2