#Freedom_and_Equality_Party
ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ህዳር 26 እና 27 ቀን 2013 ዓ/ም የሶማሌ ክልል ሸንጎ ምስረታ አካሂዷል።
ከአስራ አንድ ዞኖች ተወክለው ወደ ጅግጅጋ የሄዱ አባላት የመጀመሪያው የክልላዊ ሸንጎ ስብሰባቸውን ማድረጋቸውን ፓርቲው ገልጿል።
የክልሉ ስራ አስፈፃሚ ከሁሉም ዞኖች አንዳንድ ስራ አስፈፃሚ ተካተው እንደገና መዋቀራቸውም ተነገሯል።
ላለፉት 11 ወራት በተለያዩ የሶማሌ ክልል የተከፈቱ ቢሮዎች ስራ እንቅስቃሴ በክልል ደረጃ በጅግጅጋ ዋና መስሪያ ቤት መቀመጫ ላይ ተገምግመዋል።
እስከአሁን በክልሉ በአጠቃላይ 24 የነ.እ.ፓ. ቢሮዎች ተከፍተው ስራ ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው ያሳወቀ ሲሆን እነዚህ ቢሮዎች በክልሉ ማዕከልነት በተዋረድ እንዲሰሩ መደረጉን አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Freedom_and_Equality
ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በሳዑዲ አረቢያ በእስር ቤት እና ማጎሪያ ካምፖች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ ጠየቀ፡፡
ነእፓ አዲስ አበባ ለሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ በጻፈው ደብዳቤ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ በእስር ቤትና ማቆያ ካምፖች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ተለቀው ወደ ሀገራቸው መምጣት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ጠይቋል፡፡
በፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር አብዱልቃደር አደም ለአምባሳደሩ የተላከው መልእክት የሁለቱን ሀገሮች ከሺህ ዓመት በላይ የዘለቀ ግንኙነት አስታውሶ፣ ኢትዮጵያውያን ያሉበት እጅግ ዘግናኝ ሁኔታ የፍትህ እና የነጻነት መለያ ለሆነችው ቅድስት ሀገር የማይመጥን በመሆኑ እስረኞቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቋል፡፡
የደብዳቤው ቅጂ ለኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና ሳዑዲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተላልፏል፡፡
(ሙሉ መልእክቱ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

👍377❤22👎15👏13😱7🥰4