TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ወደ ትግል ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል።

ከንቲባው ዛሬ አመሻሹን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት ከእኛ ይጠበቃልና፤ እኔም ከሌሎች ወንድሞቼ ጋር ወደ ትግሉ ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ። በግንባር ተገኝተን ያዘጋጀነውን ስንቅ እናቀብላለን፤ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ጀግናው ሠራዊታችንን በወኔ እናበረታታለን " ብለዋል።

የአስተዳደሩ የፀጥታ ኃይሎችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ የድሬዳዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ፤ የልማትና አስተዳደራዊ ሥራዎችን በሙሉ አቅማቸው ለማከናወን ተዘጋጅተዋል ሲሉም አሳውቀዋል።

አቶ ከድር ጁሀር ፥ " መላው ነዋሪዎች አካባቢያችሁን በመጠበቅ፤ ሠራዊቱን በመደገፍና፤ ወደ ግንባር በመዝመት፤ እንዲሁም በፀሎት ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪ አቀርባለሁ። ያለጥርጥር ኢትዮጵያ ታሸንፋለች " ሲሉ ነው በተረጋገጠ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደግንባር ዘምተው ሰራዊቱን እንደሚመሩ ካሳወቁ በኃላ የተለያዩ ባለስልጣናት ፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ የስፖርት ሰዎች ጨምሮ ሌሎችም ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ እገለፁ መሆናቸው ይታወቃል።

#Teddy

@tikvahethiopia
👍3