TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባህር ዳር‼️

ከአንድ ወር ገደማ በፊት ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ጥለው የወጡ ተማሪዎች #በአማራ_ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልንመደብ ይገባል የሚል ጥያቄ ይዘው በባሕር ዳር ከተማ ሰልፍ አደረጉ። በዛሬው ሰልፍ ወደ 2500 ተማሪዎች መገኘታቸውን በቦታው የተገኘው የDW ዘጋቢ ተናግሯል። ተማሪዎቹ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተነስተው እስከ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተጉዘዋል። ሰልፈኞቹ በክልሉ መንግሥት ቢሮ ፊት ለፊት "መንግሥት የለም! መንግሥት ቢኖር ጥያቄያችንን ይመልስልን ነበር" የሚል መፈክር ማሰማታቸውን የDW ዘጋቢ ታዝቧል። የጸጥታ አስከባሪዎች ኹኔታውን በርቀት ሲከታተሉ ነበር። በአብዛኛው ጥቁር የለበሱት ተማሪዎች መንግሥት ጥያቄያችንን ይመልስልን፤ በአማራ ክልል እንመደብ" የሚል ጥያቄ በሰልፉ ላይ አሰምተዋል። የኢኖቬሽን እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ይመለሱ የሚል ምላሽ ባለፈው ሳምንት ሰጥቶ ነበር። ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑት "ሴቶች ይደፈራሉ፤ ወንዶች ይደበደባሉ" በሚል ምክንያት ነው። DW እንደዘገበው ተማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በሚገኝ ስታዲየም ተጠልለው ይገኛሉ።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍2