TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sidama

ከነገ ጀምሮ በሲዳማ ክልል የሰአት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎች ተላለፉ።

የሲዳማ ክልል ኮማንድ ፖስት ከነገ ጀምሮ ገደብ የተጣለባቸውን የሰአት እላፊ፣ የእንቅስቃሴዎች ገደብ እና ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሰረት ፦

- ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል (ታርጋ ያለው ብቻ) አንድ ሰው ጭኖ ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ከጎንና ጎን ያለበሱትን ሸራ በማንሳትና ሶስት ሰው ብቻ በመጫን እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት ፣ የህዝብ ትራንስፖርትና ታክሲዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 2 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ ይችላሉ።

- መታወቂያን በተመለከተ ፦ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉ ሀላፊዎች መታወቂያ መስጠት የማይችሉና ማንነቱን የሚገልፅ መረጃ በመያዝ ግለሰቦች ከዛሬ ጀምሮ ጊዜያዊ መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ።

- ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ፦ ከዚህ ቀደም ያስመዘገበም ያላስመዘገበም ከነገ ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በአቅራቢያው በሚገኙ የፖሊስ ተቋማት ማስመዝገብና የፈቃድ ወረቀት መያዝ ይኖርበታል።

NB: ይህን ያላደረገና ያልተመዘገበ የጦር መሳሪያ ይዞ የተገኘ ማንኛውም አካል እንደ ወንጀለኛ የሚጠየቅ ይሆናል።

- ፋብሪካዎች፣ ኢንደስትሪ ፖርኮች፣ ሪዞርቶችና አለም አቀፍ ሆቴሎች የሰራተኛ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ከፖሊስ ኮሚሽኑ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ።

- ከሲዳማ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ወደ ክልሉ የሚገቡ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መግባት አይችሉም። በእግረኞችና የቤት መኪኖች ላይ የሰዓት ገደብ ባይጣልም መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

@tikvahethiopia
👍3