TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"..ህዝቡን እያሽበርኩ በዚህ እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ ዳግም በተጠናከረ መልኩ የሀይል እርምጃ ይወሰድበታል" - ሀገር መከላከያ ሰራዊት

ከሰሞኑን ትግራይ ክልል የነበረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለምርጫው ሰላማዊነት ሲባል ወደሌላ የአገሪቱ አካባቢዎች መንቀሳቀሱን ተከትሎ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህውሓት ሚሊሻዎች ከተደበቁበት በመውጣት ሰላማዊውን የትግራይ ህዝብ ሲያሸብሩ ነበር አለ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ በሰጠው መግለጫ።

የሰራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ ፥ ሀገራዊ ምርጫውን ተከትሎ ከውጭም ከውስጥም ስጋት ስለነበር ሰራዊቱ በመንግስት ትዕዛዝ መሰረት ከትግራይ ወደ ማዕከል፣ ምስራቅ፣ ምእራብና የደቡብ የሀገራችን ክፍል እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ነበር ብለዋል።

"ይህን ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ በየጢሻው ተደብቆ የነበረው የህወሓት ሚሊሻ ህዝቡን ሲያስገድድና ሰላማዊ እንቅስቃሴውን ሲያስተጓጉል ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ በወሰደው እርምጃ ህዝብን ወደ ሰላማዊ ኑሮው መመለስ ተችሏል ሲሉም ተደምጠዋል።

ዳይሬክተሩ ፥ በክልሉ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት በመስራት ገበሬው እንዲያርስ፣ ነጋዴው እንዲነግድ፣ ተማሪዎች እንዲማሩ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል።

ይህ መልሶ የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተደረገ ባለበት ወቅት የህወሓት ሀይል ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን ፋይዳ ቢሲ ትንኮሳዎችን ከተደበቀበት እየወጣ እየተነኮሰ ይገኛል ብለዋል።

በሽብርተኝነት የተፈረጀው ቡድን ህዝቡን እያሽበርኩኝ በዚህ እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ ዳግም በተጠናከረ መልኩ የሀይል እርምጃ እንደሚወሰድበት አስጠንቅቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-06-24

#ኢፕድ
@tikvahethiopia
እየከፋ የመጣው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ስርቆት :

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ በሁምቦ ላሬና ቀበሌ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፍያ ታወርና ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የስርቆት ወንጀል በመፈፀሙ በአካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ተቋርጦ መሰንበቱን የኢትይጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የስርቆት ወንጀሉ የተፈፀመው ከወላይታ ሰብስቴሽን ተነስቶ ለሦስት የደቡብ ዞኖች አገልግሎት በሚሰጥ የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመር ላይ ሲሆን በዚህም ሁለት ታወሮች ወድቀዋል፣ 20 ታወሮች ደግሞ ብረታቸው ተገንጥሎ ተወስዷል፡፡

የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመሩን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎችን ሳይጨምር 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ ይጠይቃል ተብሏል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆቱ በተቋሙና በኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያደርስ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ችግሩ የተከሰተባቸውን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች በእንጨት ምሶሶ በመስራት ለተቋረጠባቸው ለ3ቱ ዞኖች አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡

የወላይታ ዞን ዓቃቤ ህግ በከፍተኛና በዝቅተኛ ኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የሚፈፀማን የስርቆት ወንጀል ለመከላከል በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ሲሆን በእዚህም ደርጊቱን የፈፀሙ 5 ግለሰቦች ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ማድረጉን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በስርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ 32 ግለሰቦችን በ11 መዝገቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡ #ኢፕድ

@tikvahethiopia