TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶክተር አብይ አህመድ! ለቀጠናው ሰላም የሚያዋጣው መደመር ብቻ ነው።

እስኪ ተዋደዱ! #ደቡብ_ሱዳን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደቡብ_ሱዳን

የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ም/ሚኒስትር ሀገራቸው የናይል ወንዝን በመጠቀም ሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት ዕቅድ ማዘጋጀቷን አሳወቁ።

ም/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ዳው ዴንግ ማሌክ ለናሽናል ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ ከዕርስ በርስ ጦርንት የተላቀቀችው ደቡብ ሱዳን ወደ ኢንዱስትሪ መር የገበያ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት የሚስችል ገንዘብ አላት ብለዋል።

ፕሮጀክቱ መንግስት ከነዳጅ ሽያጭ በሚያገኘው ገቢ ለመገንባት ዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑን ተገልጿል።

ደ/ሱዳን ርካሽ፣ ታዳሽና በሀገሪቱ በየጊዜው የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ መከላከል የሚያስችል የግዙፍ ግድብ ግንባታን በይፋ ለማስጀመር ዕቅድ መያዟን ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ በየወቅቱ በሚፈጠር የጎርፍ አደጋ፣ በሀይል እጥረት፣ የውሃ እጥረትና በደካማ የመሰረተ-ልማት ችግር እንደምትሰቃይ ጠቅሰዋል።

ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር የሚቻለው በቅድሚያ የሀይል አቅርቦት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማምረት ሲቻል እንደሆነና ግድቡ የሀይል ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ግድቡ ምን ያህል ርዝመት፣ ምን ያህል ውሃ መያዝና ምን ያህል ሀይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ሊኖሩት እንደሚገባ የሚሳይ መነሻ ዝርዝር ዕቅድ እና ጥናት በሀገሪቱ የመስኖ ሚኒስቴር በኩል መከናወኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ደቡብ ሱዳን ይህን ግድብ የመገንባት ሉዓላዊ መብት እንዳላት ምክትል ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው ግድብ ሚነሱ አለመግባባቶች በትብብር መንፈስ በውይይት ሊፈታ ይገባል ብለዋል።

www.thenationalnews.com/world/africa/south-sudan-poised-to-realise-nile-dam-dream-says-minister-1.1248408

#ENA

@tikvahethiopia
👍1