TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ፦

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ፣ ከአሜሪካ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት የመግለጫቸው ዋነኛ አጀንዳ ነበር፡፡

ቃል አቀባዩ ምን አሉ ?

- አሜሪካ የጣለችውን እገዳ በማስመልከት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ ነው የሚቀርብን” ማለት ያሰሙትን ንግግር በተመለከተ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ “ግለሰቦች የመናገር መብት አላቸው ፤ ይህም የግል አስተያየትና ስሜታቸው ነው” ብለዋል፡፡

- የኦሮሚያ ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ” ሲሉ የተናገሩት ንግግር የመንግስት አቋም ሳይሆን የግላቸው አስተያየት መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልፀዋል።

- በውጭ ጉዳይ ደረጃ “ጉዳዩን የማጋጋል ፍላጎት የለንም” ብለዋል ፤ “የተፈጠረው ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ በጋራ ወዳጆቻችን በኩል እየተነጋገርን ነው ያለነው” ሲሉ አሳውቀዋል።

- የሴናተር ጂም ኢንሆፌ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል የተፈጠረውን ጉዳይ ለመፍታት እየተኬደ ያለበት የዴፕሎማሲ መንገድ አካል ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል ፤ "የአሜሪካ አቋም ይቀየራል ብለን ነው የምናምነው ፣ መቼና እንዴት የሚለው ግን እነሱን የሚመለከት ነው” ብለዋል።

- ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መገናኘታቸውን እና “ውጤታማ ጉብኝት” አድርገዋል ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-06-02

#አልዓይን

@tikvahethiopia
"...በሰሜን የገጠመን ግጭት እስካሁን ከገጠሙን ከሁሉም የከፋው ነው" - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢፌድሪ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያለፉት ሦስት ዓመታት ዋና ዋና ንግግሮቻቸውን የያዘ ''ዐሻራ'' የተሰኘ መጽሐፍ የምረቃ ስነስርዓት እና በኢፕድ 80ኛ ዓመት በዓል ላይ ተገኝተው ነበር።

በዚህም ወቅት ላይ የ3 ዓመታቱን ፈተናዎች በተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡

ከተናገሩት መካከል ፦

" ተደጋጋሚ ችግር ያሳለፍንባቸው ያለፉት ሶስት ዓመታት ፣ በፊት ከነበሩት 10 ዓመታት ጋር ሲነፃፀሩ ቢያንስ ከጂኦ ፖለቲካ አንፃር የከፉ ጊዜያት ናቸው።

በሰሜን የገጠመንን ግጭት አንዳንዶች ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ ከካራማራው ጦርነት ጋር ሊያነፃፅሩ ይሞክራሉ ፣ ነገር ግን ወታደርም ስለሆንኩ ከሁሉም የከፋው ግጭት ነው።

ከጣልያን ጋር ስንዋጋ በጎራዴም ቢሆን እኛ ጎራዴያችንን ይዘን እነሱም በመሳሪያቸው ተዋግተናል። በኤርትራ እና ካራማራውም እኛም እነሱም ባለን ነው የተዋጋነው።

አሁን ግን የነበረው ውጊያ የኛን ትጥቅ እና የኛን መከላከያ በማፍረስ ነው ከኛ ጋር የነበረው ወጊያ።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆነን በሰላሙ ጊዜ ተጀምረው መጠናቀቅ ካልቻሉ 10 ትላልቅ የስኳር ፋብሪካዎች 7ቱን አጠናቀናል፤ ሌሎች ብዙ ፕሮጀክቶችንም እንዲሁ።"

#አልዓይን

ፎቶ : የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@tikvahethiopia