TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የካቲት11

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የተመሰረተበት የየካቲት 11 ክብረ በዓል ላይ ከ150,000 በላይ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሏል። በበዓሉ ላይ የሚገኙ ታዳሚዎችን ለማስተናገድና በዓሉን በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#የካቲት11

45ኛው ዓመት የየካቲት 11 በዓል በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እመከበሩን ቀጥሏል። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ተከታትለን እናጋራለን።

[PHOTO : TPLF]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

ህወሓት የተመሰረተበት 45ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት 08/06/12 ዓ/ም ከተለያዩ የሀገሪቱ ህብረተሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች የነፃነት ችቦ የተለኮሰባትን ደደቢት መጎብኘታቸውን ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

በጉብኝቱ የፌደራሊስት ሓይሎች ተወካዮች ፣ የምሁራን ፎረም ፣ የወጣቶች ፎረም ፣ ያገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም ከ 9 የአገራችን ክልሎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም የኢህአዴግ ነባር አመራሮች በድምር ከ300 ሰው በላይ ላይ ተሳትፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

45ኛው ዓመት ህወሓት የተመሰረተበት የየካቲት 11 በዓል የተለያዩ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊስት ኃይሎች፣ የፌደራልና የክልል መንግስት አመራሮች፣ ነባር ታጋዮች እና ምራሁራን በተገኙበት የፓናል ውይይት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በሌላ መረጃ፦

45 ተኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን የመጡ እንግዶች ጋር የፓነል ዉይይት ተካሂዷል፡፡

#ትግራይቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመቐለ ትግራይ ስታዲየም በመከበር ላይ ይገኛል። ማለዳ ላይ በዓሉን በማስመልከት በሰማዕታት ሀውልት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ነባር ታጋዮች የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በአሁኑ ሰዓት የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በትግራይ ስታዲየም እየተከበረ ሲሆን፥ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ነባር ታጋዮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

#TIGRAYCOMMUNICATION #FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia