#JAWARMOHAMMED #OFC
[በዋዜማ ሬድዮ]
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ተሰምቷል።
የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት በፊት ገልጿል። ይሁንና የዜግነቱ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲን ተቀላቅሎ መታወቂያም ወስዷል።
ጉዳዩን በተመለከት ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ድብዳቤ ፅፎ ማስረጃ የጠየቀ ሲሆን ፓርቲው በበኩሉ ጃዋር ማስረጃ እንዲያቀርብ በደብዳቤ አሳስቧል። የፓርቲው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ይህን መረጃ አረጋግጠዋል። “የኛ አባል ሲሆን ለምን ይህ ጥያቄ እንደተነሳ ባይገባኝም እኛ ደብዳቤ ፅፈንለታል” ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና።
እንዴት ለዜግነቱ ማረጋገጫ ሳያቀርብ በህግ ባልተፈቀደ መልኩ ጃዋር መሀመድ ፓርቲውን እንዲቀላቀልና መታወቂያ እንዲወስድ እንደተፈቀደለት ለተነሳላቸው ጥያቄ መረራ ጉዲና ሲመልሱ ” እኛ የምናውቀው ኢትዮጵያዊ መሆኑን ነው፣ የሀገሩን ቋንቋ ይናገራል፣ ፊቱም ኢትዮጵያዊ ይመስላል፤ መንግስትም ይህን ያውቃል” ሲሉ ቀልድ አዘል ምላሽ ስጥተዋል።
በጃዋር ዜግነት ላይ ከመንግስት የሚነሳው ጥያቄ ፖለቲካዊ ፍላጎትንም ያካተተ ሊሆን ይችላል ያሉት መረራ ጉዲና ጃዋር በቅርብ ዜግነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ እንደሚመጣ ተስፋ እንደሚያደርጉና ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድም በጊዜው ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
[ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia