TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀሰተኛ መረጃዎች⬆️

በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

TIKVAH-ETHIOPIA ሰዎች በሰውነታቸው ተከባብረው የተሳባሰቡበት ቤት ነው። ቤተሰባችን ውስጥ ፈፅሞ መሰዳደብ አይቻልም፤ የሰዎችን አመለካከት ማንቋሸሽ አይቻልም፤ በብሄራቸው፣ በእምነታቸው ላይ አፀያፊ ቃላትን መናገር አይቻልም። የቤተሰባችን አባልት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ከተለያዩ ውጭ ሀገራት የተሰባሰቡ ናቸው።

ይህ ገፅ ትልቁ ስራው አባላቱ መረጃዎችን እርስ በእርስ መለዋወጥ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት ነው። የቤተሰቡ አባላት በያሉበት ሆነው የሚያዩትን ነገር ከማጋራት በተጨማሪ ከተለያዩ ሚዲያዎች ዜናዎች #ተመርጠው የሚጋሩበት መድረክ ነው። አንዳዶች TIKVAH-ETHን እንደትልቅ ሚዲያ፣ ከጀርባው ደጋፊ እንዳለው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ድምፅ አድርገው ይቆጥሩታል። ይህ በጣም ስህተት ነው ገፁ የሁላችንም ነው። የባለስልጣኑም፣ ፓለቲከኛውም፣ አርቲስቱም፣ ጋዜጠኛውም፣ አክቲቪስቱም፣ የግል ሰራተኛውም፣ ተቀጣሪውም፣ ተማሪውም፣ የህዝብ አሰተዳዳሪውም፣ የሀይማኖት መሪውም፣ የሀገር ሽማግሌውም ...የሁሉም ቤት ነው TIKVHA-ETH! ከጀርባው ሆኖ የሚደግፈውም የለውም!

ወደዋናው ጉዳይ ስገባ...

ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ አሳዝኖናል። ያሰራጩ አካላትም እርምት ይወስዳሉ ብለን እጠብቃለን። ሀይማኖታዊ ጉዳዮች sensitive ናቸው። የሚሰራስጩ መረጃዎችም ጥንቃቄ ካልታከለባቸው እልቂትን የሚፈጥሩ ሊሆኑ ይችላሉ። /የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ እንዴት እንደዋለ ከዚህ በፊት ነግሬያችሁ ነበር/። ይህ ማለት ግን መረጃ ይደበቅ፣ ይታፈን፤ ተድበስብሶ ይቅር፣ ፖለቲከኞሽ በሚዲያ እየወጡ ይዋሹ ማለት አይደለም።

የሚሰራጩ መረጃዎች ግን መዘዛቸው ምንድነው፣ ሌላ ቦታ ተጨማሪ እልቂት ይፈጥራሉ ወይ?፣ የሰዎች ስሜት ላይስ ምን ይፈጥራል፣ ማህበረሰቡ ላይስ የሚፈጥረው ምንድነው? የሚሉትን ነገሮች ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለባቸው። መረጃዎች እውነት እንኳን ቢሆኑ በምን መልኩ ይቅረቡ፣ የሚለው ሊታሰብበት ይገባል። ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ያሉበትን ሁኔታ የምታውቁት ነው። መረጃዎችን መደበቅ አያስፈልግም ነገር ግን ሲሰራጩ ተጨማሪ ችግር በሚፈጥር እና በማጋጋል ወይም ደግሞ ሌሎችን ለጥፋት በሚያነሳሳ መልኩ ሊሆን አይገባም።

መቼም የተሳሳቱ መረጃዎች በሀገራችን ውስጥ ያመጡትን መዘዞች ከናተ የሚደበቅ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም በሀይማኖት ጉዳዮች በፖለቲካው የሚሰራጩ መረጃዎች ያመጡትን መዘዝ አይተናል። እኛ መረጃዎችን እንደወረደ የምንቀበልበት አቅም ያለን ህዝቦች መስሎ አይሰማኝም፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል በተለይ አሁን ያለንበት ሁኔት። ያለችን ትንሽ ሰላም በእጃችን ከወጣች እመኑኝ ዳግም አናገኛትም!! እናንተም አስተዋይ ናችሁና ሲሰራጩ የምታገኟቸው መረጃዎች ማጣራት እንዳትዘነጉ ከማን? ለምን? ተላለፉ፤ እኔ ሼር ሳደርገው ምን ይፈጠራል? አላማው ምን ይሆን ብለን እንጠይቅ። አንዳንዶች በውጭ ሀገር ስላሉ ምናልባት እኛ ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ላያውቁት ይችላሉ፤ ማህበረሰቡም የሚሰማውን ነገር ሁሉ እንዴት እንደሚቀበለው ብዙም የተረዱት አይመስለኝም።

ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳያረጋግጡ እና ሆንብለው የሚያሰራጩትም ልቦና ይስጣቸው ከማለት ውጭ ምንም ማለት አይቻልም!!

በመጨረሻም...

/TIKVAH-ETH/ ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ #የሚያሳዝኑ ልብ የሚሰብሩ መረጃዎች ሲጋሩበት ነበር። እዚሁ ሀገራችን የኦርቶዶክስም፣ የወንጌላውያን አማኞች ቤተ እምነቶች ሲቃጠሉ፤ ካህናት ሲገደሉ፣ መስጊድ ሲቃጠል፣ አባቶች ሲገደሉ...ብቻ በምድር ላይ አሉ የሚባሉ መጥፎ ነገሮች ሁሉ ቀርበውበታል። አዲሱ አመት ግን ክፉ ማንሰማበት፤ የሰላም፤ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ፣ መስጊድ ፈረሰ፣ መስጊድ ተቃጠለ፣ ሰዎች በብሄራቸው ጥቃት ደረሰባቸው፣ በሃይማኖታቸው ተጠቁ፣ የሚሉ ዜናዎችን የማንሰማበት ሰላማዊ፣ የፍቅር እብሮነታችን የሚጠነክርበት ዓመት እንዲሆን በእውነት ከልብ ከልብ እመኛለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia