TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ፣ የመድሃኒት ዕጥረት መባባሱን የሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር ገልጿል፡፡ በተለይ የአስም፣ ስኳር እና ደም ብዛት መድሃኒቶች ዕጥረት አሳሳቢ መሆኑን የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ለሸገር ራድዮ ተናግረዋል፡፡ መድሃኒቶቹ ባንድ ወር ጊዜ ውስጥ #ያልቃሉ፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው መድሃኒት መጠንም በጣም #አነስተኛ ነው፡፡ ሐኪሞች የሚያዟቸው መድሃኒቶች በሕጋዊ መንገድ የገቡ ወይም ትክክለኛ መድሃኒት መሆን ይሁኑ አይሁኑም በቂ ማረጋገጫ የለም፡፡ መንግሥት ለመድሃኒት ግዥ በቂ የውጭ ምንዛሬ እንዲመድብም ማኅበሩ ጠይቋል፡፡

Via ሸገር 102.1/wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር

ባለዲግሪው መፃህፍት አዟሪ በብልሽት ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ ለስራ እንዲሆነው ከከተማ አስተዳደሩ ተበረከተለት!

ከተመረቀ በኋላ ለአራት አመታት መፃህፍት በማዞር ህይወቱን ሲመራ የነበረው ወጣት አንዷለም ይስሃቅ ከከተማ አስተዳደሩ ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ በኢ/ር ታከለ ኡማ ተበርክቶለታል።

ወጣቱ ደርሶበት በነበረው የአእምሮ ህመም ችግር ሳይበገር እና ስራ ጠባቂ ሳይሆን እራሱን ለመለወጥ ያደረገው ጥረት ለብዙዎች አርአያ የሚሆን እንደሆነም ተነግሯል።

በጥቂት ጊዚያት ውስጥም በከተማዋ ያለ አገልግሎት የቆሙ ሌሎች 700 የሚሆኑ አንበሳ የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተንቀሳቃሽ ሱቆች በመቀየር በከተማዋ ለሚገኙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ይህ ተግባር በአንድ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ የመፍጠር ግዙፍ እቅድ አካል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በችግሮች ሳይበገሩ ራሳቸውን ለመቀየር እየሞከሩ ያሉ ወጣቶችን ለማበረታታት አላማ ያደረገ ተግባር ነው።

Via #mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia