This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ከተሰጣቸዉ እዉቅናና ፍቃድ ዉጪ የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ የግልና የመንግስት ኮሌጆችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡ ኤጀንሲዉ ከእዉቅናዉ ዉጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡
በአዲስ አበባና አካባቢዋ 18 የግል ኮሌጆችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶችን መዝጋቱን አስተዉቋል፡፡ እንዲሁም 4 የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከእዉቅናዉ ዉጪ ከግል የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር ሲሰጡ የነበረዉን አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን የኤንጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ሞታ ተናግረዋል፡።
በተለይም በግል ዘርፍ የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አብዛኞቹ ደረጃቸዉን ባለጠበቁ የትምህረት ቅጥር ግቢ ዉስጥ እንደነበር ጠቁመው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ኤጀንሲዉ ቁርጠኛ አቋም መያዙንም ምክትል ዳሬክተሩ አስታዉቀዋል።
Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia