TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥያቄው_ምላሽ፦ TIKVAH-ETH የተመሰረተው እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በሃምሌ 19/2009 ዓ/ም ነው። TIKVAH በተመሰረተበት ወቅት የቤተሰቡ አባላት 20 አይደርሱም ነበር። የነበሩትም #ንቁ ተሳታፊ አልነበሩም። ዛሬ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኘው የቤተሰባችን አባል ከ320 ሺ በላይ ነው። በተመሰረተበት ወቅት ቀለል ያሉ የመዝናኛ ነክ ጉዳዮችንና ፎቶዎችን ያቀርብ ነበር። ለጥቂት ጊዜ ትውውቅ ከተደረገ በኃላ በወቅቱ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነበረው ችግር ሳቢያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተማሪ ድምፅ ሆኖ አገልግሏል።

TIKVAH ማለት #ተስፋ ማለት ነው!

√እኛ ማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርበት፤ ሰውነቱ ሲከበር ብሄሩ፣ ቋንቋው፣ ባህሉ፣ አመለካከቱ፣ እምነቱ የሚከበርበት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ አስተማማኝ ደህንንነት እና ሰላም ያለባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ ማንም ሰው በአመለካከቱ የማይገፋበት ለሁሉም ዜጎች እኩል የሆነች ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን!

√እኛ አይደለም ለኢትዮጵያዊ በምድር ላይ ላለሰው ሁሉ የምትሆን ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ ዜጎቿ የማይበደሉባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

#ተስፋችን_ደግሞ_በፍጡር_ሳይሆን_በፈጣሪ_ብቻ_ነው!

ይህ አቋማችን የዛሬ ሳይሆን የነበረ፤ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው!! #ETHIOPIA

🏷ይሄ ቤተሰብ "የኢትዮጵያ ተስፋ" ነው ብለን እናምናለን!! በመነጋገር የሚያምን ከጥላቻ የራቀ፤ ስድብ የሚፀየፍ አንድ ጠንካራ የሆነችን ሀገር ለመገንባት ዘውትር የሚተጋ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ስብስብ ነው

ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia