TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ገንደ ውሃ‼️

የገንደ ውሀ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ #አራጋው_ሰንታ ዛሬ ጠዋት ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በስልክ የተናገሩት፦

•እንደተባለው የህብረተሰቡ አቋም የሱር ኮንስትራክሽን መኪኖች ይፈተሹልን ነበር ምክንያቱም በህብረተሰቡ ዘንድ ድርጅቱ ትልልቅ የጦር መሳርያዎችን ከሱዳን ወደሌላ ክልልሎች ያስተላልፋል የሚል ጥርጣሬ ነበር። እነሱ ግን ይባስ ብለው በመከላከያ ታጅበው መጡ።

•በመሀል መከላከያዎች ህዝቡ ላይ መተኮስ ጀመሩ። አንድ ህፃን እና ሎሎች ሁለት ሰዎች እኛ ከተማ ላይ ሞተዋል። ኮኪት ከተማ ላይም የሞቱ ሰዎች አሉ። እነዚህ በሙሉ ንፁሀን ዜጎች እና ምንም መሳርያ ያልታጠቁ ነበሩ። ኮኪት ከተማ ላይ ግን የሞቱ የመከላከያ አባት እንዳሉ ሰምቻለሁ።

•ትናንት በተካሄደ ሰልፍ ህዝቡ ሱር ይፈተሽልን፣ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ እና ሰላም ይስፈን ብለው ጠይቀዋል።

በተጨማሪ...

የኮኪት ከተማ ነዋሪው ይመር ስለ ማክሰኞው ግድያ ለጋዜጠኛ ኤልያስ በስልክ የተናገረው፦

•የሱር መኪናዎች ገንደ ውሀ ላይ ህዝቡን አዘናግተው እንዳለፉ ሲወራ ህዝቡ ኮኪት ከተማ ላይ ሆኖ ጠበቃቸው። ይህ የሱር አካሄድ ጥርጣሬን ጫረ።

•ኮኪት ከተማ አቅራቢያ አንድ ድልድይ አለ። መከላከያዎች ድልድዩን አልፈው ብቅ እንዳሉ እና ህዝቡን እንዳዩት መተኮስ ጀመሩ። በዚህም ከአንድ ቤት ሶስት ሴቶች ተገድለዋል። በአጠቃላይ እኛ ከተማ ብቻ አምስት ሰው ሞቶ ስምንት ሰው ቆስሏል።

•ከከተማው አንድ ወይም ሁለት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለ እና አንደኛ ጎራ በተባለ ተራራ ላይም ከባድ መሳርያ ተተኩሶ ሲነድ ነበር።

•ህዝቡ በመጀመርያ ድንጋይ ሲወረውር ነበር። ከዛ በሁዋላ ግን አስፓልት ላይ የቆመ ሰው ሲመታ አንድ ሁለት ጥይቶች ወደ መከላከያ ተተኩሰዋል። የሞቱ ወታደሮች እንዳሉ ግን አልሰማንም።

•በመጨረሻ መኪኖቹን ኑ ፈትሹ ተብሎ ሲፈተሹ የተባለው መሳርያ አልተገኘም። አዳር ላይ ምን ሲሰሩ እንዳደሩ ግን አይታወቅም። አሁን መከላከያዎች #ወጥተዋል፣ ድባቡም #የተሻለ ነው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነቀምት🔝

የወለጋ ዩኒቨርስቲ Civil Engineering #ተመራቂ ተማሪዎች ዛሬ GC Announcement ቀንን አክብረዋል። ወጣቶቹ ቀኑን ያከበሩት "ሠውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!" በሚል ከ7ኛ-10ኛ ለሚማሩ ተማሪዎች አጋዥ መፀሀፍትን በስጦታ በማበርከትና ነቀምት ከተማን #በማፅዳት ነው። ሁሉም በአቅሙ #የሚችለውን ቢያደርግ ሁላችንም #የተሻለ ቦታ እንደርሳለን ሲሉ ተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፋዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል #የተሻለ እና #አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ሕጋዊ ትጥቅን ‹‹የማስፈታት ሥራ እንደተጀመረ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ›› ተብሏል፡፡ ተጨማሪውን ያንብቡ👇

https://telegra.ph/አማራ-ክልል-ETHIOPIA-07-04