TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አየር መንገዱ ተሸለመ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እኤአ የ2019 የአፍሪካ #ምርጥ_የጭነት አየር መንገድ አገልግሎት ሽልማትን ተቀዳጀ። ሽልማቱን ያዘጋጀው የኤር ካርጎ ኒውስ ተቋም በዓለም አቀፍ ደረጃ የካርጎ ዜናዎችን በመዘገብ፣ የኢንዱስትሪውን መሪዎች ቃለ መጠይቅ በማድረግና ኢንዱስትሪውን የተመለከቱ ትንታኔዎችን በመስራትና ለአለም አቀፍ የአየር ጭነት አገልግሎት ሰጪዎች ሪፖርቶችን በማዘጋጀት የታወቀ ነው። በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው የአየር ጭነት አገልግሎት አቅራቢው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማቱን ሚያዚያ 18 በእንግሊዝ ለንዴን ተቀብሏል።

“ቤስት ካርጎ ኤር ላይን 2019 “ተሸላሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ሽልማቶችን መቀዳጀቱንም ዘገባው አስታውሷል።
በኤር ካርጎ ኒውስ የሚዘጋጀው “የአመቱ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ “ የሚሰኘው ሽልማት በዘርፉ የተከበረና ከፍተኛ እውቅና ያለው ሽልማት ነው። ሽልማቱን አስመልክቶ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረ ማርያም”ይህነን የተከበረ ሽልማት በመቀዳጀታችን ከፍ ያለ ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia