TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አብን‼️

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት #ብርቱካን_ሚደቅሳ ለfbc እንዳረጋገጡት፥ ለአብን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ከጥር 28 2011 ዓ.ም ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) #የሀገር_አቀፍ_የፖለቲካ_ፓርቲ የምዝገባ እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለሁለት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህጋዊ እውቅና መስጠቱንም ወይዘሪት ብርቱካን ተናግረዋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ሰኔ 3 2010 ዓ.ም በይፋ ተቋቁሞ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia