TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ለማ መገርሳ‼️

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ በአዳማ ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፈቱ፡፡

በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው የተከፈቱ የልማት ፕሮጀክቶች ከ442 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደረገባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ከተመረቁ የልማት ስራዎች መካከል 2 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ፣3 ነጥብ 1 የጠጠር መንገድ፣ 348 አባወራዎች ሚኖሩበት እና 10 ሱቆችን በውስጡ የያዘ የጋራ መኖሪያ ቤት ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የቁም እንስሳት የገቢያ ማዕከል፣ናማ ኮምፖስት የተሰኘ ቀሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ማዕከል ፣ አቦ ፓርክ የመናፈሻ ቦታ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤት በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው ተከፍተዋል፡፡በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት 20 የሚሆኑ የተለያዩ የልማት ስራዎች ናቸው የተመረቁት፡፡

በተመረቁት የልማት ስራዎች ከ1 ሺህ 700 በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ተብሏል፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በ2011 በጀት አመት 35 አዲስ እና 34 ነባር ፕሮጀክቶችን ከ530 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ ወደ ስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን ከንቲባው አቶ መስፍን አሰፋ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia