TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬆️

የቡራዩ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ በንፁሃን ነዋሪዎች ላይ የተፈፀመውን ድርጊት #በማውገዝ ዛሬ ሰልፍ አካሂደዋል።

የከተማዋን ነዋሪ የማፈናቀሉ ተግባር የቡራዩን ከተማ #ወጣት በአጠቃላይ ነዋሪውን አይወክልም ብለዋል።

ሰለፍኞቹ ከተማዋ የሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ናት በማለትም ተፈናቃዮቹ ወደ ከተማቸው #እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖቻቸውንም መልሶ #ለማቋቋም ዝግጁ መሆናቸውንም ነው ያስታወቁት።

በተጨማሪም ሰልፈኞቹ በአዲስ አበባ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት የማድረስ ተግባርን እንደሚያወገዙ በመግለፅ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆም ጠይቀዋል።

©ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ. ለተወሰነ ጊዜ ተዘጋ‼️

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተስተጓገለ ያለውን የትምህርት ክፍለጊዜ ለማስተካከል ለጊዜው የመማር ማስተማሩ ሂደት ተቋርጦ ተማሪዎች ወደ የቤተሰቦቻቸው #እንዲመለሱ መወሰኑን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር #ለሚ_ጉታ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካቋረጡ 31 ቀናት ሆናቸዋል።

ይህንኑ ቀናት ሁሉ ባክኖ የመጀመሪያውን መንፈቀ ዓመት የመማር ማስተማር እቅዱን ማሳካት ስለማይቻል እንደ አዲስ ትምህርቱን የካቲት 25 ቀን እንዲጀመር በሴኔቱ ተወስኗል።

የባከነውን የትምህርት ክፍለጊዜ እንደ አዲስ አስተካክሎ ለመጀመርና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማረጋገጥ ለጊዜው ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መወሰኑን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

ተማሪዎቹ ከአንድ ወር በላይ ትምህርታቸውን ያቋረጡት ዩኒቨርሲቲው የገባልን ቃል አልፈፀመም በሚል ሰበብ እንደነበር አስታውሰዋል።

የተማሪዎቹ ጥያቄ የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የትምህርት እድል እንደሚመቻችላቸው እንዲሁም የሥራ እድል ትስስር ከኢንዱስትሪዎች ጋር እንደሚፈጠርላቸው ቃል ተገብቶልን ነበር የሚል ነው።

በተጨማሪም ላፕቶፕ ኮምፒዩተር እንደሚሰጣቸው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት የነበሩት የውጭ ዜጋ ቃል ገብቶልናል የሚል ጥያቄ እንደሚያነሱም ዶክተር ለሚ አመልክተዋል።

መንግስት ሁኔታዎችን አይቶና ገምግሞ የሀገሪቷን አቅም መሰረት ያደረገ መፍትሔ እንደሚፈልግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣የቦርድና የዩኒቨርስቲው አመራሮች ባሉበት በተካሄደው ውይይት ቢገልፅም ተማሪዎቹ ለመቀበል ሳይፈልጉ ቀርተዋል።

በዚህም ምክንያት ከአንድ ወር በላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን በማስተጓጎል አንዳንድ ተማሪዎች ከጊቢ ወጥተው ለተለያዩ ሱሶችና አልባሌ ተግባራት እየተጋለጡ መሆኑን ጠቁመዋል።

”በተቋሙ ውስጥ የምግብ፣የመኝታና ተጓዳኝ አገልግሎት እያገኙና የሀገር ሀብት እየባከነ እንደፈለጉ መሆን ስለማይቻል ለጊዜው የመማር ማስተማር ሂደት በማቋርጥ ተማሪዎች ወደየ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ወስነናል “ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከጥር 12/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎች ቅጥር ጊቢውን ለቀው እንዲወጡና ወደ የቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ጠቅሰው የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው ከነሱ የተለዩበትን ዓላማ ብቻ ከዳር እንዲያደርሱ የማድረግና የመምከር ቤተሰባዊ ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

በሴኔቱ ውሳኔ ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚመለሱትና በአዲስ መልክ ተመዝግበው ትምህርታቸውን የሚጀምሩበት የካቲት 25 እና 26/2011 ዓ.ም. እንደሆነ ያስታወሱት ዶክተር ለሚ “ነገር ግን የባከነውን የትምህርት ክፍለጊዜ ለማካካስ በማሰብ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መልሰን ለመጥራት ርብርብ እያደረግን እንገኛለን“ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው እየተስተጓጓለ ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስተካከል የወሰደው እርምጃ አግባብ መሆኑን የገለጸው ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሮንክስና ኮሙዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል የአምስተኛ ዓመት ተማሪና የተማሪዎች ተወካይ ፍፁም ቱጁባ ነው።

በ2007 ዓ.ም. በወቅቱ ተቋሙ ሲመሩ በነበረው የውጭ ዜጋ በአፍ ደረጃ የላፕቶፕ ኮምፒዩተሮችን ጨምሮ የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ እንደሚሰጣቸው የተገባውን ቃል አሁን ካልተፈፀመልን አንማርም ብሎ ትምህርት ማቋረጥ ትክክል እንዳልሆነ ጠቅሷል፡፡

አሁን ላይ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው ራሳቸውን እንዲያዩና እንዲፈትሹ የሚያደርግ የእርምት እርምጃ በመሆኑ እንደሚደግፈው ተናግሯል።

”በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲረጋገጥ የተማሪ ቤተሰቦች ጭምር የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው” ብለዋል።

ተማሪዎችም ቢሆኑ ከፖለቲካ ግፊትና አስተሳሰብ ወጥተው የመማር ግዴታቸውን እየተወጡ የወጡለትን ዓላማ ሳይጎዱ መብታቸውን መጠየቅ እንደሚገባቸውም ተማሪ ፍፁም መልዕክቱን አስተላልፏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia