TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬆️

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከነዋሪዎቹ ጋር #የሰላም እና #የልማት ዉይይት እያካሄደ ነዉ። ከቀናት በፊት በከተማዋ ተከስቶ የነበረዉን #አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ ከአገር የሽማግሌዎች፤ ወጣቶች ከተለያዩ አደረጃጀቶች ከተወከሉ ነዋሪዎች ጋር በዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ ምክክር እየተካሄደ ነዉ። የከተማዋ ከንቲባ አቶ #ሰለሞን_ፈየ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና የዜጎች ተዘዋዉሮ መስራት እና መኖር መብት እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ‼️

በአዳማ ከተማ የሕብረተሰቡን #የልማት ጥያቄዎች #ሊመልሱ የሚችሉና 500 ሚሊየን ብር የወጣባቸው ከ20 በላይ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ዛሬ #እንደሚመረቁ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአዳማ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ #መስፍን_አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በመርሃ ግብሩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን፤ ፕሮጀክቶቹ ከዚህ ቀደም ይነሱ የነበሩ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንደሚፈቱም ይታመናል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia