TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹በማህበራዊ ሚዲያ #የጥላቻ ንግግሮችን ለሚያወጡ ሰዎች #ህግ እያወጣን ነው፡፡››

◾️▪️ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ አህመድ▪️◾️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌስቡክ‼️

የማይናማር #ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ መዋሉን ሪፖርት ጠቆመ።

ፌስቡክ በማይናማር ከ18 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት። ፌስቡክ ለበርካቶች ዋነኛው ወይም ብቸኛው የመረጃና የዜና ምንጭ ነው።

የፌስቡክ አስተዳደሮች “በማይናማር እየገጠመን ያለውን ችግር ለመቅረፍ እየሠራን ነው። ሆኖም ብዙ ይቀረናል” ብለዋል።

ባለፈው ዓመት የሮሂንጋ ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ የሃገሪቱ ጦር ራክሂን በምትባለው ግዛት ላይ
መጠነ ሰፊ ጥቃት ሰንዝሮ ነበር።

በሺዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን ሲያጡ፤ ከ700 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት ሃገር ባንግላዲሽ ተሰደዋል። በሮሂንጋውያን ላይ የአስገድዶ መድፈር፣ የእርሻ መሬትን መቃጠልና መሰል በደሎች ሮሂንጋውያን በማይናማር (በርማ ተብላ ትጠራ በነበረው) ሃገር ውስጥ እንደ ስደተኛ ይቆጠራሉ። በመንግሥት እና በተቀረው ሕዝብ
ለበርካታ አስረት ዓመታት ተገልለዋል።

ቢዝነስ ፎር ሶሻል ሪስፖንሲቢሊቲ (Business for Social Responsibility -BSR) ያቀረበው ባለ 62 ገጽ ገለልተኛ ሪፖርት ”በማይናማር ግጭትና ጥላቻን ማባባስ ለሚፈልጉ ቡድኖች ፌስቡክ መጠቀሚያ ሆኗል” ይላል።

ሪፖርቱ፤ ፌስቡክ #የጥላቻ_ንግግርን በተመለከተ ያለውን ፖሊሲ እንደገና ሊከልሰው ይገባል ሲልም አክሏል።

ምንጭ፦ ቫይስ ኒውስ(በጌጡ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1