TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የሰላም ውድ ዋጋ በግልፅ የሚስተዋለው ላፍታ ሲጓደል ነው!" ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን
~~~~~<>~~~©

ዘላቂ የሃገር ሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን መወጣት እንደሚገባው ም.ጠ.ሚ/ር አቶ #ደመቀ_መኮንን አሳሰቡ።

ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና የሰላም አቀንቃኝ የሆኑትን አቶ #ኦባንግ_ሜቶን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በሰሜን አሜሪካ "ግድግዳውን እናፍርስ፤ ድልድዩን እንገንባ" በሚል መርህ ከወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የቀረበውን ጥሪ አቶ ኦቦንግ በአክብሮት ተቀብለው ወደ እናት ሃገራቸው በመመለሳቸው ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ ምስጋና እና አድናቆት ቸረዋል።

አቶ ኦባንግ በሃገር ቤት የወራት ቆይታ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች እየተዘዋወሩ ሃገራዊ ለውጡ ቀጣይነቱ እንዲጎለብት ለትውልዱ የሚያስተላልፉት አነቃቂ መልዕክት ተቀባይነት ያለውና ሊጠናከር እንደሚገባ አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመከላከል እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚያደርገውን ሃገራዊ ጥረት ለማገዝ ፤ አቶ ኦባንግ በትውልዱ ዘንድ ያላቸውን ሰፊ የተደማጭነት እና የተቀባይነት ዕምቅ አቅም መንዝረው በቀጣይ እንዲደግፉ ም.ጠ.ሚ/ሩ
ጠይቀዋል።

የሰላም ውድ ዋጋ በግልፅ የሚታወቀው ላፍታ ሲጓደል በመሆኑ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ ሰፊ የግንዛቤ እና የንቅናቄ ስራዎች እንደሚያስፈልጉ አቶ ደመቀ አስረድተዋል።

አቶ ኦባንግ በበኩላቸው በም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ በተደረገላቸው አቀባበል እጅግ መደሰታቸውን በመግለጽ፤ ተስፋ የፈነጠቀው ሃገራዊ የለውጥ ጉዞ ዘላቂነት እንዲኖረው የግል ጥረታቸው እንደሚያጠናክሩ አረጋግጠዋል።

በውጭ ሃገር "ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ" የተሰኘ ድርጅት በመስራችነትና በዋና ዳይሬክተርነት የሚንቀሳቀሱት አቶ ኦባንግ፤ በሃገር ቤት በሚኖራቸው ስምሪት ድርጅቱ በሰብዓዊ መብት እና በሰላም ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

በቀጣይ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ትርጉም ያለው ስራ መስራት ፍላጐት እንዳላቸው
አቶ ኦባንግ ገልጸዋል።

በሃገር ውስጥ ህጋዊ ዕውቅና እና ምዝገባ አጠናቀው ከመንግሥት ጋር በቅንጅት ለመስራት ሰፊ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንም አብራርተዋል።

በመጨረሻም ለሃገራዊ ሰላም ግንባታ የጋራ ጥረት እና ዘላቂ ውጤት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia