TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

በአዲስ አበባ ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ወጣቶች በያዝነው ሳምንት #እንደሚለቀቁ ተገለፀ።

ወጣቶቹ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 8 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለFBC እንደተናገሩት፥ በመንግስት በኩል በቁጥጥር ስር ለዋሉት ወጣቶቹ እስካሁን የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል።

በጦላይ ለአንድ ወር እራስን ከወንጀል ስለማራቅ እና ተያያዠ ስልጠናዎችን ለመስጠት የተያዘው የጊዜ ሰሌዳም የፊታችን #ሀሙስ ይጠናቀቃል ብለዋል ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል።

አስፈላጊው ሎጀስቲክስ ሚሟላ ከሆነ ወጣቶቹ የፊታችን ሀሙስ ካልሆነ ደግሞ እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ የሚለቀቁ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ዘይኑ ወጣቶችን አስተምሮ ከመልቀቅ ባለፈ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ስራ አጥ የሆኑትን በጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።

በከተማዋ በነበረው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ውለው ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ 1 ሺ 204 ወጣቶች ሲሆኑ፥ ከነዚህ ውስጥ በወንጀል የተጠረጠሩት 83 ወጣቶች በህግ የሚጠየቁ ናቸው ብለዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia