TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ዳውሮ ዞን⬆️

በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ዛሬ ማለዳ ላይ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ12 ሰዎች #ህይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከፍተኛ #ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የወረዳዉ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የመሬት መንሸራተቱ በወረዳዉ ጉዛ ቀበሌ ዘማ መንደር በሶስት መኖርያ ቤቶች ላይ መከሰቱን የጽህፈት ቤቱ ኃለፊ ሻምበል አልታዬ አለሙ ገልፀዋል፡፡

በአደጋው ከሞቱት 12 ሰዎች መካከል በህብረተሰቡ ተሳትፎ የ10ሩ አስክሬን የተገኘ ሲሆን፥ የሁለቱ አስክሬን ባለመገኘቱ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉን አራት ግለሰቦች ወደ ተርጫ ሆስፒታል በመውሰድ የህክምና ዕርዳት እንዲያገኙም እየተደረገ ነዉ፡፡

በአደጋዉ ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን፥ በቀጣይ ጊዜያትም በስፍራዉ ያሉ ቤቶች ጥንቃቄ ካልተደረገላቸዉ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክላሲ ውሀ⬆️

ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ #ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ በመረጋገጡ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውለው የንግድ ሚኒስቴር አሳሰበ።

የሚኒስቴሩ የገበያና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት እንደተናገሩት፥ በላይ ኢንዱስትሪያል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚያመርተው ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ ተረጋግጧል።

ከ2007 እስከ 2009 ዓመተ ምህረት በተደረገ የጥራት ፍተሻ ምርቱ በተደጋጋሚ የጥራት ጉድለት የታየበት በመሆኑ እንዲታገድና ከገበያ #እንዲሰበሰብ መደረጉንም ነው ዳይሬክተሩ ያስታወሱት።

ድርጅቱ የምርት ጥራቱን እንዲያስተካክል የውዴታ ግዴታ እንዲፈርም በመደረጉ ማስተካከሉ ተረጋግጦ ታህሳስ 2009 ዓ.ም እገዳው ተነስቶለት ወደ ስራ ገብቷል።

ሚያዚያ 2010 ዓመተ ምህረት በተደረገ የገበያ ኢንስፔክሽን ስራ የምርቱ ናሙና ተወስዶ በተደረገው የቤተ ሙከራ ፍተሻ የታሸገ ውሃው በድጋሚ የጥራት ደረጃውን ያላሟላ ሆኖ ተገኝቷል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ክላሲ የታሸገ ውሃን ከመጠቀም #እንዲቆጠብ የንግድ ሚኒስቴር ለfbc በላከው መግለጫ አሳስቧል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia