TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ልዩ_ዜና ታንዛንያ⬇️

በታንዛንያ ደቡባዊ ክፍል የምቤዬ ግዛት ፖሊስ የአንድ ሰፈር ሰዎችን በሙሉ #በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ ሰዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ለአካባቢው የውሃ አገልግሎት ለመስጠት የተዘረጋውን የቧንቧ መስመር ከጥቅም ውጪ አድርገውታል በማለት ነው።

የእስር ትእዛዙን ያስተላለፉት የግዛቲቱ ፖሊስ ዋና ኃላፊ በበኩላቸው የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን የውሃ መስመር በማበላሸታቸው ምክንያት በቁጥጥር እንደዋሉ ገልፀዋል።

በአካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት የደረሰበት የውሃ አገልግሎት መስጫ በብዙ ሺ ዶላሮች ወጪ የተሰራ ሲሆን፤ እስካሁን የአካባቢው ተመራጭን ጨምሮ ብዙ የአካባቢው ነዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ሁላችንም በጉዳዩ ስላልተሳተፍን የምርመራው ሂደት ንጹህ ሰዎችን እንዳያካትት እንሰጋለን እያሉ ነው።

ፖሊስ በበኩሉ ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ መገልገያዎችን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ብሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ይህንን ማድረግ ስላልቻሉ ለዚህ ውሳኔ እንደደረሰ ገልጿል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia