TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ልዩ_ዘገባ - ይነበብ⬇️

ቀደም ሲል ወደ ሀገር ቤት የገቡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጉዳይ አስፈፃሚዎችን በዓየር ለማጓጓዝ ለሆቴልና ትራንስፖርት መንግስት ዳጎስ ያለ ወጪ ማውጣቱ ተሰምቷል።

ለግለሰቦቹ የየዕለት የሆቴል መስተንግዶና ሌሎች ወጪዎች ከዕለት ዕለት እየናረ መምጣቱን የሚናገሩት የመንግስት የሰራ ሀላፊዎች ወጪው ለሀገር ሰላምና ዕርቅ ሲባል የሚከፈል በመሆኑ ጉዳዩን መንግስት በሆደ ሰፊነት ሲመለከተው ቆይቷል።

አሁን ግን የወጪው መናር ያሳሰባቸው ሆቴሎች መንግስት ክፍያ እንዲፈፅም መጠየቃቸውንና እየቀረበ ያለው የገንዘብ መጠን አነጋጋሪ መሆኑን ለዋዜማ ራድዮ ቅርብ የሆኑ የአዲስ አበባ ምንጮች ተናግረዋል።

የገንዘብ ወጪውንና ምን ያህን እንግዶች በመንግስት መስተንግዶ እየተደረገላቸው እንደሆነ ራድዮ ጣቢያው የጠየቃቸው ምንጮዥ ሆቴሎች ሀገራዊ ፋይዳውን በመረዳት ቅናሽ ቢሰጡንም ተሰተናጋቾቹ በርካታ እንግዶች የሚጎበኟቸው በመሆኑና የቢሮ አገልግሎት የሚጠቀሙም ስላሉ ወጪውን ከፍ ማድረጉን አስረድተዋል። የገንዘቡን መጠን መናገር ግን እንደማይደፍሩ ተናግረዋል።

አሁን ቢያንስ ሀምሳ ሁለት ያህል እንግዶች በመንግስት እየተሰተናገዱ ሲሆን ከሶስት ወር እስከ አንድ ሳምንት የቆይታ ዕድሜ አላቸው።

አንዳንዶቹ ለጊዜው ከሆቴል ውጪ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ይቆዩና ተመልሰው እንደሚመጡ አንዳንዶቹ ደግሞ አዲስ አበባ ቤተሰብ ስለሌላቸው በቋሚነት የሆቴሉ እንግዶች ሆነው ቀጥለዋል። የፀጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውም ሆቴል መሆኑን እንደሚመርጡ ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና ከሰሞኑ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች መንግስት ለጉዞና ለሆቴል ወጪያቸውን ለመሸፈን ያቀረበላቸውን ግብዣ ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ተሰምቷል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በአሜሪካ በነበረው ውይይት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በአንድ አውሮፕላን መመለስ እንደሚችሉ የተነገራቸው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ማናቸውንም ወጪ ራሳቸው እንደሚችሉና ለመመለስ ዝግጅት እንደሚያሰፈልጋቸው ገልፀው የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ግብዣ ከምስጋና ጋር ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች በቀናት ጊዜ ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ያቀናሉ። ለአቀባበሉም ዝግጅት እየተደረገ ነው። አመራሮቹ ወደ ሀገር ቤት ሲጓዙ ለብቻቸው አይደለም፣ ከፍ ያለ ቁጥር ያለው የድርጅቱ ደጋፊና አባል ከባህር ማዶ አብሮ ይጓዛል። በመላዊ ኢትዮጵያ ያሉ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች አዲስ አበባን ያደምቋታል። በክልል ከተሞችም የአቀባበል ስነስርዓት ይካሄል።

©WazemaRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1