TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC

" በዚህ ኮሚሽን ተገዶ የሚኖር፣ ተገፍቶ የሚወጣ ኮሚሽነር መኖር የለበትም እኔን ጨምሮ " - ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ትላንት ዓመታዊ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከጋዜጠኞች ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች አንዱ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እና በኮሚሽኑ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግብ ገብረሐዋርያ ሥራ የለቀቁበት ምክንያት ምን እንደሆነ የሚመለከት ይገኝበታል።

ኮሚሽነሩ በምላሻቸው ኮሚሽነሮቹ፣ " ሥራ የለቀቁበት ምክንያት እስካሁን ባለኝ መረጃ በራሳቸው ምክንያት ነው። በግል ምክንያት ይልቀቁ እንጂ በዚህ ኮሚሽን ተገዶ የሚኖር፣ ተገፍቶ የሚወጣ ኮሚሾነር መኖር የለበትም እኔን ጨምሮ። ባልተመቼው ጊዜ ያልተመቼው ሰው ሊለቅ ይችላል " ብለዋል።

" የአዲሱ ኮሚሽነር የአመራር ችግር ነው " የሚሉ ጉዳዮችን እየሰሙ መሆኑን የተናገሩት ዋና ኮማሽነር
ብርሃኑ፣ " በዚህ ላይ እኔ መልስ መስጠት አልችልም፤ አፕሮፕሬት የሆኑት አካል እነርሱ ራሳቸው ናቸው። ከዚህ በዘለለ ኮሚሽነር ይህን አድርገው ነው ብለው መልስ መስጠት ያለባቸው ራሳቸው ናቸው ፤ በኔ በኩል የምለው ይሄን ብቻ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ " በአማራ ክልል ይፈጸማሉ ለሚባሉ የድሮን ጥቃቶች " ኮሚሽኑ የጥቃቱን ሁኔታ አጣርቶ እንደሆን ሲጠየቁም " በሪፓርታችን የተወሱኑ አሊጌሽኖች አሉ፤ ድሮን አይደለም፤ የከባድ መሳሪያ ጥቃቶች ናቸው " ብለዋል።

" በመከላከያ አስገድዶ ምልመላ አለ " በሚል ለሚነሳው የመብት ጥሰት ምላሽ እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ ከመከላከያ ሚናስቴር ጋር ውይይት መደረጉን፣ በአማራ ክልል በኩል አስገድደው ካልሆነ በስተቀር ሚኒስቴሩ እንዳላስገደደ እንደገለጸላቸው፣ የኦሮሚያ ክልልም " አንድም ሰው በግዴታ መልምለን ያስገባነው የለም " በሚል ሪፖርት እንዳደረገ አቶ
ብርሃኑ ገልጸዋል።

የበቴ ጉርጌሳ ግድያ ምርመራ ጉዳይ ከምን እንደደረሰ ተጠይቀውም፣ " እነዚህ ኬዞች ከኔ ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ተያይዘው የሚነሱ አይደሉም። በወቅቱ የነበሩ የሥራ ኃላፊዎች በቂ መልስ ሊሰጡ የሚችሏቸው ናቸው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ተሻሻሉ " የሚባሉ " የሪፎርም " ስራዎችን እንዴት እንደገመገሙት ሲጠየቁም፣ " የሲቪክ ሶሳይቲ ህጉ ባለፈው ሰኔ ጀምሮ ለማሻሻል እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል፤ ተገኝተንም የኛን ሀሳብ አስቀምጠናል፤ ያን ተከትሎ ግን ሰፊ የውትወታ ስራዎች በተለያዩ አካላት እየተሰሩ ነው ያሉት፤ አሁን ባለው ሁኔታ ሪፓርታችንን ለዘብ የሚያደርግ ነው ባለኝ መረጃ " ብለዋል።

" ሰኔ 16 ቀን እና ከሦስት ቀናት በፊት የተላከልኝ ድራፍት ለውጥ አለው " ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ፣ " የሲቪክ ሶሳይቲ ዐዋጁ በዚህ ደረጃ እየተደማመጥን ምህዳሩ በማይጠብ መልኩ የምንሄድ ከሆነ አንድ ውጤት አድርጌ ነው የማየው " ሲሉም መልሰዋል።

የሚዲያ ዐዋጅንም "እንዲሻሻል" ምክረ ሀሳብ እንዳቀረቡ የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ " የሚዲያ ነጻነቱን በማይጥስ መልኩ እንዲተገበር ጥንቃቄ አድርጉ ብለናል " ነው ያሉት።

ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን በዓለም አቀፍ ሳይሆን በኢትዮጵያ ደረጃ እንደሚታይ ከዓመታት በፊት ተነግሮለት የነበረው ጉዳይ ከምን እንደደረሰ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመዳኘት የጸደቀው የሽግግር ፍትህ ፓሊሲ ወደ ኢምፕልመንቴሽን እንደገባ፣ በፍጥነት ግን እየሄደ እንዳልሆነ፣ በረቂቅ ደረጃ እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
655😡183😭23🤔16🙏9😱7🥰6😢3🕊3👏2