TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 በሕይወት የመኖር ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል። ይህን የገለጸው ዛሬ በላከልን ዓመታዊ ሪፖርቱ ነው። " በ2017 በሕይወት የመኖር መብት ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን የሚያሳዩ በርካታ ክስተቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተስተውለዋል " ሲል ገልጿል። በግጭት ዐውድ ውስጥ በቆዩ ወይም በግጭት ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች ፦ - በመንግሥት…
#Amhara
አማራ ክልል !
(ከኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርት)
🔴 የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰውን የታጠቀ ቡድን (ፋኖ)ን " ትደግፋላችሁ፣ ትቀልባላችሁ" በማለት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸው ተረጋግጧል።
⚫️ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን አባላት (ፋኖ) በበቀል ስሜት በወሰዷቸው እርምጃዎች እና " ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መንገድ አሳይታችኋል ፤ ሰዎችን ጠቁማችሁ አስይዛችኋል '' በማለት በሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፡፡
➡️ በአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ወንጀላ ቀበሌ ሰኔ 5 ለሰኔ 6/ 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ሌሊት ላይ በመንግሥት ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን ፋኖ አባላት መካከል የተደረገውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ የመንግሥት ኃይሎች በ5 ሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፡፡
➡️ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ አባላት መካከል ሰኔ 17/2016 ዓ.ም. ሰሜን ጎጃም ዞን፤ አዴት ከተማ ላይ በተካሄደ የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ተገድለዋል። በመንግሥት ኃይሎች ከ3 ወር በፊት ተይዘው ካምፕ ውስጥ ታስረው የነበሩ 3 ፋኖ አባላት ተገድለዋል። የፋኖ አባላት በቁጥጥር ሥር አውለዋቸው የነበሩትን ቢያንስ 8 የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ተገድለዋል፡፡
➡️ የፋኖ አባላት ጎንዘር ቋራ ወረዳ በአብተጋሆ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 23 ሲቪል ሰዎችን አፍነው ወደ ቴዎድሮስ ከተማ በመውሰድ የተወሰኑት ሲመለሱ ሌሎችን ገድለዋል፡፡
➡ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ ጣርማ በር ወረዳ፣ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ “ሾላ ሜዳ'' በተባለች ቦታ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም. የመንግሥት ኃይሎች እና የፋኖ አባላት መካከል በተካሄደ ግጭት በተለያዩ ምክንያቶች በ15 ሰዎች ላይ ግድያ ተፈጽሟል፡፡
➡️ ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም. በሰሜን ወሎ ዞን፣ ጉባ ላፍቶ ወረዳ፣ ውድመን ቀበሌ ላይ የትጥቅ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት ኃይል በተተኮሰ የጦር መሣሪያ 7 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
➡️ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም. ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ በሚንቀሳቀሰው የፋኖ አባላት 17 የአካባቢው ነዋሪዎችን ይዘው በመውሰድ በማግስቱ ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከእነዚህ ውስጥ 4 ሰዎች ተገድለው አስክሬናቸው ተጥሎ ሲገኙ የቀሩት ሰዎች ደግሞ ገንዘብ በመክፈል ከቀናት በኋላ ተለቀዋል፡፡
➡️ በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ፣ ዶማ በተባለ አካባቢ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂ አባል ቆስሎ 2 ወንድሞቹ ሊያነሱት ሲሄዱ 3ቱም ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል።
➡️ በሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት ዓባይ ቀበሌና በአካባቢው በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ አባላት መካከል ከነሐሴ 6 እስከ 7/2016 ዓ.ም. ከተካሄደ ውጊያ ተከትሎ በመንግሥት ኃይሎች 7 ሰዎች ተገድለዋል።
➡️ ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ቀበሌ 5 በግ ተራ አካባቢ የመንግሥት ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በ2 ሰዎች ላይ የሞት እና 10 የአካል ጉዳት ደርሷል።
➡️ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ አዘዞ ጸዳ ክፍለ ከተማ፣ ጸዳ ቀበሌ ጤና ጣቢያ አካባቢ 1 የመንግሥት የጸጥታ አባል ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የመንግሥት ኃይሎች ቢያንስ 11 ሰዎችን መግደላቸው ተረጋግጧል።
➡️ መስከረም 6/2017 ዓ.ም. በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደባርቅ ከተማ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ አባላት መካከል ከተካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች ቢያንስ 29 ሰዎች ተገድለዋል።
➡️ ከመስከረም 6 እስከ 7/ 2017 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ መካከል በነበረው የትጥቅ ግጭት በሁለቱም ወገን በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ሕፃናትን እና ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 10 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። ተጎድቶ ሆስፒታል ከገቡ ሰዎች 1 ሰው ሕይወቱ አልፏል፡፡
➡️ መስከረም 8/2017 ዓ.ም. በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ስናን ወረዳ በፋኖ አባላት ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት አካባቢ 2 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን ከመኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ የገደሏቸው ሲሆን በሌሎች 4 መምህራን ላይ ድብደባ ፈጽመዋል። በመምህራኑ ላይ የተፈጸመው ግድያ እና ድብደባ በ2017 ዓ.ም. ትምህርት ለማስጀመር ካደረጉት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ነው።
➡️ መስከረም 23/ 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ጉና በጌምድር ወረዳ፣ ክምር ድንጋይ ከተማ በመንግሥት ኃይሎች የተተኮሰ የጦር መሣሪያ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ግቢ ላይ በማረፉ 2 የቤተሰቡ አባላት ሲገደሉ ሌሎች 2 ሕፃናት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
➡️ መስከረም 26/ 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን፣ በቋራ ወረዳ የፋኖ አባላት 8 ሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፡፡
➡️ ኅዳር 11/ 2017 ዓ.ም. በማእከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ ለምባ አርባይቱ ቀበሌ፣ አርባ ተንሳይ ጎጥ በመንግሥት ኃይሎች ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የመንግሥት ኃይሎች 3 ሰዎችን ገድለዋል፡፡
➡️ ታኅሣሥ 3/2017 ዓ.ም. በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ገነተ-ማርያም ቀበሌ አርክን በተባለ ቦታ 5 ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡
➡️ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቡ ወረዳ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች መጋቢት 2/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ 3 ሰዎችን (የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፣ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ እና ሾፌር) ለሥራ ጉዳይ ከወረዳው ዋና ከተማ ቢስቲማ ወደ ቦኬክስ ሲሄዱ ልዩ ቦታው ጠቢሳ ከሚባል ቦታ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለዋቸዋል።
➡️ መጋቢት 8/ 2017 ዓ.ም. በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች የይካሆ ቀበሌ ነዋሪዎችን " ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ፋኖን ትዋጋላችሁ " በሚል የጦር መሣሪያ ለመውሰድ ሲሞክሩ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ታጣቂዎች መጋቢት 11/2017 ዓ.ም. በድጋሚ ወደ ይካሆ ቀበሌ በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 6 ሰዎችን ገድለዋል።
➡️ መጋቢት 11/ 2017 ዓ.ም. በሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ የፋኖ አባላት ከቀኑ 6:00 እስከ 7:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ከተማው ዘልቀው በመግባት 4 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን ጨምሮ 6 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል።
➡️ መጋቢት 28/2017 ዓ.ም. ከቀነ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደርዞን፣ ፎገራ ወረዳ፣ ዓለም በር ከተማ የፋኖ ታጣቂዎች ዘልቀው በመግባት 2 የአባይ ባንክ የጥበቃ ሠራተኞችን ገድለዋል። አባይ ባንክ ላይ ዘረፋ ፈጽመዋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በፀደይ ባንክ ላይ የዘረፋ ሙከራ አድርገዋል።
➡️ ግንቦት 2/2017 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጭልጋ ወረዳ፣ ኳበር ሎምጌ ቀበሌ የፋኖ ታጣቂዎች 2 ሰዎች ገድለዋል፤ 4 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፤ የቤት እንስሳ ዘርፈው ወስደዋል፣ 7 የመኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም 34 የሚሆኑ የመንደሩ አባወራዎችን አፈናቅለዋል።
(ሙሉ የአማራ ክልል መረጃ ከላይ በምስሉ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

😭1.25K❤1.24K😡80🕊64💔48👏27🥰20🤔20🙏10😱5😢4