TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

ከእገታ ማስለቀቂያ 2 ሚሊዮን ብር የተጠየቀበት ህፃን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተገድሎ ተጥሎ ተገኘ።

ከ5 ቀናት በፊት የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳባጉና ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ የሆነው ህፃን ናኦድ ተኽላይ ብርሃነ በአጋቾች ታፍኖ መወሰዱንና አጋቾቹ ለማስለቀቅያ 2 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸው የሚጠቅስ በህፃኑ ፎቶ የታጀበ ፅሁፍ በበርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ሲዘዋወር ነበር።

ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ወደ ህፃኑ ቤተሰብ ደውለው ነው የማስለቀቅያ ብሩን የጠየቁት ይላል ሲዘዋወር የቆየው ፅሁፍ።

ዛሬ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም የተሰማው ግን እጅግ አስደንጋጭ መርዶና ከሰውነት የወጣ የጭካኔ ተግባር ነው።

ህፃን ናኦድ ተኽላይ በጭካኔ ተገድሎ የፀጥታ አካላት በተገኙበት አስክሬኑ በፍሳሽ መተላለፍያ ቦይ ተጥሎ ተገኝቷል።

የሟች ህፃን ናኦድ ተኽላይ አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከእንዳስላሰ-ሽረ የመረጃ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
5😭6.46K992💔932😡316😢84🕊79😱57🙏35🤔28🥰10👏7