TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Peace🕊

" 35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል " - አሜሪካ

ከ1980ዎቹ አንስቶ ጦርነት ውስጥ የነበሩት አርሜኒያና አዘርባጃን በአሜሪካ አማካኝነት የሰላም ስምምነት ፈጽመዋል።

የአዘርባጃን ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሌቭ እና የአርሜኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሽኒያን የፈረሙት ስምምነት ለአስርት አመታት የዘለቀውን ግጭት ያስቆማል ተብሏል።

የሰላም ስምምነቱን የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሸማግለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሰላም ስምምነቱን " ረጅም ጊዜ የወሰደ ታሪካዊ ስምምነት ነው " ብለውታል።

ሁለቱ ሀገራት በአወዛጋቢው የናጎርኖ ካራባህ ግዛት ጦርነት ውስጥ እንደነበሩ ያስታወሱት ትራምፕ ግጭቱን " እስከወዲያኛው ይወገዳል " በማለት ተናግረዋል።

ትራምፕ፣ " 35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል " ብለዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ሀገራት የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የንግድ ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲጀመሩ እና ለተፈፃሚነቱ አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

Via @ThiqahEth
577🕊114👏62🤔26😡9🥰7😱6😢5💔4🙏3