TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በአንዳንድ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚስተዋለው ባህሪ የነገ ተስፋቸውን ሊያጨልም የሚችል የሙችል በመሆኑ ሊታረምና በወላጆች ዘንድም ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊደረግበት ይገባል !! " - ፖሊስ

" ታግተናል " በማለት ወላጆቻቸውን 500 ሺህ ብር የጠየቁ ታዳጊዎቸ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

አጋችና ታጋች በመምሰል የማታለል ወንጀሉን የፈፀሙት አራቱ ተጠርጣሪዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ናቸው።

ልጆቹ ለሁለት ቀናት ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሲዝናኑ ቆይተው ገንዘብ ሲያጥራቸው በመመካከር ለቤተሰብ ስልክ ይደውላሉ።

ወንዶቹ አጋች ሴቶቹ ደግሞ ታጋቾች በመሆን ለሴቶቹ ቤተሰቦች በደወሉት ስልክ 5 መቶ ሺ ብር የጠየቁ ሲሆን የሴት ወላጆች አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ጥቆማ ሠጥተዋል።

ፖሊስም መረጃዎችን በማሰባሰብ አራቱንም ተጠርጣሪዎች ካሉበት ቦታ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ችሏል፡፡

የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በወቅቱ ሴት ልጆቻቸው መታገታቸውን ሲሰሙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተው እንደነበር ተናግረው ፖሊስ ላከናወነው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

" በልጆች አስተዳደግ ዙርያ የቤተሰብ ኃላፊነት ከፍተኛ ነው " ያለው ፖሊስ " በአንዳንድ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚስተዋለው ባህሪ የነገ ተስፋቸውን ሊያጨልም የሚችል በመሆኑ ሊታረምና በወላጆች ዘንድም ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊደረግበት ይገባል " ሲል ገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
585😡137🤔92😭52👏40💔30🙏15😢12🕊11😱10🥰6