TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በሰላም ተጠናቋል ! እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የተገኘበት ዓመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላምና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳውቋል። ኮማንድ ፖስቱ የትራፊክ አደጋን ጨምሮ ምንም ዓይነት ያጋጠመ ችግር እንዳልነበረ ገልጿል። #ኤፍኤምሲ @tikvahethiopia
#Hawassa

በሰላም ተጠናቋል !!

በየአመቱ ሐምሌ 19 የሚከበረው የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በድምቀት፣ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።

በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው መላው የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና ቀርቧል።

ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡ የፀጥታ ግብረሃይል እና ባለድርሻ አካላት ሁሉ ተመስግነዋል።

ከበዓሉ ጋር ተያይዞ በዕለቱ በተሰየመው ጊዜያዊ ችሎት የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ በፀጥታ ግብረ ኃይል እጅ ከፍንጅ የተያዙ 03 ተጠርጣሪዎችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ወንጀል ድርጊት በተያዘው ሪከርድ ከ3 ዓመት እስከ 13 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።

በዓሉን አስመልክቶ ለቀጣይ ቀናት ቆይታቸውን ሀዋሳ ለሚያደርጉ እንግዶች ቆይታቸው የሰመረ እንዲሆን የተመኘው የክልሉ ፖሊስ የእንግዶችን ደህንነት እንደሚያስጠብቅ አረጋግጧል።

መላ ነዋሪዎቿ በፍቅር ፣ በመከባበር ፣ በመተሳሰብ እና በአንድነት በሚኖሩባት ሀዋሳ በየዓመቱ ታህሳስ 19 እና ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን በተገኘበት ይከበራል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.9K🙏276🕊48🥰34😡17😭16👏13🤔11😱6😢6