TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ_ዓመታዊ_የሰብአዊ_መብቶች_ሁኔታ_ሪፖርት_ከሰኔ_ወር_2016_ዓ_ም_እስከ_ሰኔ_ወር_2017_ዓ.pdf
#ኢትዮጵያ🇪🇹
በሕይወት የመኖር ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል።
ይህን የገለጸው ዛሬ በላከልን ዓመታዊ ሪፖርቱ ነው።
" በ2017 በሕይወት የመኖር መብት ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን የሚያሳዩ በርካታ ክስተቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተስተውለዋል " ሲል ገልጿል።
በግጭት ዐውድ ውስጥ በቆዩ ወይም በግጭት ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች ፦
- በመንግሥት ኃይሎች፣
- በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች፤
- ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እንዲሁም በእርስ በእርስ ግጭቶች በሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት እንደደረሰ አመልክቷል።
በአማራ ክልል በአብዛኛው አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች (ፋኖ) መካከል ከ2015 ዓ.ም. መጨረሻ ወራት ጀምሮ በቀጠለው የተራዘመ የትጥቅ ግጭት ዐውድ ውስጥ በተፋላሚ ወገኖች የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንደቀጠሉ ገልጿል።
በክልሉ በተራዘመ የትጥቅ ግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች የግጭቱ አካል ያልነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት እንደተዳረጉ አመልክቷል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ግጭት ሲካሄድባቸው በቆዩ ቦታዎች የመንግሥት ኃይሎች በሚቆጣጠሩበት ወቅት " ፋኖን ትደግፋላችሁ፣ ትቀልባላችሁ '' ያሏቸው ሰዎች ላይ ግድያ የፈጸሙ ሲሆን፤ መኖሪያ ቤቶችን በእሳት በማቃጠል ጭምር የተፈጸሙ ጥቃቶች ተመዝግበዋል፡፡
የታጠቂ ቡድኑ ("ፋኖ'') አባላት በበቀል ስሜት በወሰዷቸው እርምጃዎች እና " ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መንገድ አሳይታችኋል፤ ሰዎችን ጠቁማችሁ አስይዛችኋል " በማለት በሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፡፡ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዳይመለሱ ማስፈራራታቸውን፣ ወደ ሥራቸው የተመለሱ ሠራተኞች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን፤ በተለያዩ አካባቢዎች በመግባት ዘረፋ ማድረጋቸውን፤ በእሳት በማቃጠል ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማድረሳቸውን እና ነዋሪዎችን ማፈናቀላቸውን ኢሰመኮ ባከናወናቸው ምርመራዎች እንዳረጋገጠ አሳውቋል።
ኦሮሚያ ክልልን በሚመለከትም በተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎችና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) መካከል ከሚደረገው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንደቀጠሉ ኢሰመኮ ገልጿል።
በተለያዩ ምክያቶች በሰዎች ላይ የሞት፣ የአካል እና የንብረት ጉዳት ደርሷል፡፡
የመንግሥት ኃይሎች በአንዳንድ አካባቢዎች " ለኦነግ ሽኔ ድጋፍ ታደርጋላችሁ፤ መንገድ ታሳያላችሁ " በሚል በወሰዱት እርምጃ በሰዎች ላይ የሞት ጉዳት ደርሷል፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች በተለያየ ምክንያት በተወሰዱ እርምጃዎች በሰዎች ላይ የሞት፣ እገታ፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ደርሷል፡፡
ከተለያዩ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ከተማ የሚጓዙ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን በማስቆም የሚፈጽሟቸው አገታዎች በ2017 የቀጠሉ ሲሆን፤ አጋቾች ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ ክፍያ በመጠየቅ፤ ገንዘብ ለመክፈል ባልቻሉ ታጋቾች ላይ ግድያን ጨምሮ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽመዋል፡፡
ሙሉ ሪፖርት https://tttttt.me/tikvahethiopia/99053
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤598😭256😡29🙏24💔20👏18🕊17😱5🥰4😢4🤔2