#Sidama
" ተከራይተዉ በሚኖሩበት ቤት ነዉ ሞተዉ የተገኙት ! " - የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኮሚኒኬሽን
የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሙሉነህ ተክሉ በአለታ ወንዶ ከተማ ተከራይተው በሚኖሩበት ቤት ውስጥ እራሳቸውን አጥፍተው መገኘታቸውን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ቄዲዳ ሻመና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ኃላፊዉ ዛሬ ጠዋት ቢሮ ገብተዉ ባለጉዳይ ጭምር ሲያነጋግሩ እንደነበርና ምሳም ከጓደኞቻቸዉ ጋር በልተዉ ወደ ቤታቸዉ መሄዳቸዉንና ከቀኑ 8 ሰዓት አከባቢ ይህ ጉዳይ መሰማቱንም ገልፀዋል።
ከአማሟታቸዉ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን የገለፁት ኃላፊዉ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ' በግምገማ ምክንያት ነዉ ' የሚሉና ሌሎችም መረጃዎች ከእዉነት የራቁና በቅርቡ የዞና መንግስት ያካሄደዉ ምንም አይነት ግምገማ አለመኖሩን ገልፀዋል።
አቶ ሙሉነህ ተክሉ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ከመሆናቸው በፊት የአለታ ጩኮ ከተማ ከንቲባ ሆነዉ ሲሰሩ መቆየታቸውንና ከስራ ባልደረቦቻቸዉና ከመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ጋር ተግባብተው ሲሰሩ እንደነበር አቶ ቄዲዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኃላፊው አሟሟት ጋር በተያያዘ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያን አዛዥን ለማነጋገር ሞክሮ ጉዳዩ አሁናዊና መረጃ የማደራጀት ስራ ላይ መሆናቸውን በመግለፅ በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታዉቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHwassa
@tikvahethiopia

❤588😭560💔42🤔36🕊29😢22🙏17👏8😱8🥰6