TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Attention🚨

በነሀሴ ወር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በረዶ የቀላቀለና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታውቋል።

ኢኒስቲትዩቱ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ የእርጥበት መብዛት ጋር ተያይዞ በረባዳማ አካባቢዎች ፦
- የውሃ በሰብል ላይ መተኛት፣
- የመሬት አቀማመጡ ከፍታ ባላቸውና ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የመሬት መንሸራተትና በጎርፍ መጠቃት ሊያጋጥም እንደሚችል ተገልጿል።

እርጥበት በሚበዛባቸው አካባቢዎች የሰብል በሽታ እና የአረም መስፋፋት ሊከሰት ስለሚችል አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት ሰብሎች በጎርፍ እንዳይጠቁ እና በማሳ ላይ ውሃ እንዳይተኛ የጎርፍ መቀልበሻዎችንና ከማሳ ውሰጥ ውሃን ማንጣፈፊያ ቦዮችን ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል።

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ደግሞ አልፎ አልፎ በሚኖረው ተደጋጋሚ ከባድ ዝናብ ቅጽበታዊ ጎርፍ የማስከተል እድል ይኖረዋል ተብሏል።

Photo - Mehal Meda / Matip Tikvah Ethiopia Family Mehal Meda

@tikvahethiopia
1310🙏40🕊21😭17😱8😡8🤔4🥰3