#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የከተማዋ ካቢኔ በ4 ኛ አመት የስራ ዘመኑ በ11 ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የጤና ባለሞያዎችን የጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ በሚመለከት የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።
በቢሮው ሃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ተፈርሞ ለ 11 ዱም ክፍለ ከተሞች የተላከው እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ባለ አራት ነጥብ ደብዳቤ ከ2018 ዓ/ም በጀት አመት ጀምሮ ለጤና ባለሞያዎች ጥቅማ ጥቅሞቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይጠይቃል።
በዚህም መሰረት ተግባራዊ እንዲሆኑ የተወሰኑት ጥቅማጥቅሞች :-
1. የትርፍ ሰዓት ክፍያን በሚመለከት የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት አገልግሎት ክፍያ አፈፃፀምን መሰረት ባደረገ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን።
2. የጤና ባለሙያዎች፣ የትዳር አጋራቸው እና ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆቻቸው ቅድሚያ በሚሰሩበት የጤና ተቋም ፣ቀጥሎ በሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ።
3. ከዚህ ቀደም በቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮጀክት በጊዚያዊነት የተቀጠሩ የቤት ለቤት፣ የወላጆች እና አሳዳጊዎች ምክር ሰጪ ሰራተኞች በቢሮው፣ በክፍለ ከተማ እና ጤና ጣቢያዎች ላይ የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች እና ኮኦርዲኔተሮች አሰራሩን ጠብቀው ቋሚ ሰራተኞች እንዲሆኑ።
4. የኑሮ ውድነቱን ጫና ለማቃለል በሁሉም የጤና ተቋማት ውስጥ የሸማቾች ህብረት ማህበራት ሱቆች በማቋቋም በመንግስት ድጎማ የሚቀርቡ ምርቶችን የጤና ባለሞያዎች በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው መወሰኑን ደብዳቤው ይገልጻል።
በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩት ጥቅማ ጥቅሞች ከ 2018 ዓም በጀት አመት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ተፈጻሚ እንዲሆንላቸው ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እና ሃላፊዎች መመሪያ መሰጠቱን ቲክቫህ ከደብዳቤው ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia

❤678😡192🙏53😢22🤔18🕊6👏3😱3💔3😭3