#AddisAbaba
በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው።
አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል።
በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ተቋማት የትኞቹ ናቸው ?
- ንግድ ቢሮ፣
- ገቢዎች ቢሮ፣
- መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣
- መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣
- ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን፣
- ህብረት ስራ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ በተጠቀሰው መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።
@TikvahethMagazine @tikvahethiopia

😡1.39K❤1.23K👏283😭124🤔43💔31🙏28🕊27😱23🥰14😢1
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የከተማዋ ካቢኔ በ4 ኛ አመት የስራ ዘመኑ በ11 ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የጤና ባለሞያዎችን የጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ በሚመለከት የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።
በቢሮው ሃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ተፈርሞ ለ 11 ዱም ክፍለ ከተሞች የተላከው እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ባለ አራት ነጥብ ደብዳቤ ከ2018 ዓ/ም በጀት አመት ጀምሮ ለጤና ባለሞያዎች ጥቅማ ጥቅሞቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይጠይቃል።
በዚህም መሰረት ተግባራዊ እንዲሆኑ የተወሰኑት ጥቅማጥቅሞች :-
1. የትርፍ ሰዓት ክፍያን በሚመለከት የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት አገልግሎት ክፍያ አፈፃፀምን መሰረት ባደረገ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን።
2. የጤና ባለሙያዎች፣ የትዳር አጋራቸው እና ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆቻቸው ቅድሚያ በሚሰሩበት የጤና ተቋም ፣ቀጥሎ በሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ።
3. ከዚህ ቀደም በቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮጀክት በጊዚያዊነት የተቀጠሩ የቤት ለቤት፣ የወላጆች እና አሳዳጊዎች ምክር ሰጪ ሰራተኞች በቢሮው፣ በክፍለ ከተማ እና ጤና ጣቢያዎች ላይ የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች እና ኮኦርዲኔተሮች አሰራሩን ጠብቀው ቋሚ ሰራተኞች እንዲሆኑ።
4. የኑሮ ውድነቱን ጫና ለማቃለል በሁሉም የጤና ተቋማት ውስጥ የሸማቾች ህብረት ማህበራት ሱቆች በማቋቋም በመንግስት ድጎማ የሚቀርቡ ምርቶችን የጤና ባለሞያዎች በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው መወሰኑን ደብዳቤው ይገልጻል።
በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩት ጥቅማ ጥቅሞች ከ 2018 ዓም በጀት አመት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ተፈጻሚ እንዲሆንላቸው ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እና ሃላፊዎች መመሪያ መሰጠቱን ቲክቫህ ከደብዳቤው ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia

❤819😡220🙏63😢25🤔22🕊9👏8😭6💔5😱4
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ አንዳንድ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽ/ቤቶች ታጥፈዋል።
የከተማዋ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት በከተማ አስተዳደሩ የማእከል ፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አደረጃጀቶች ውጤታማነት ላይ ጥናት ሲያካሄድ መቆየቱንና በጥናቱ መሰረት አንዳንድ አደረጃጀቶች እንዲታጠፉ መወሰኑን ውሳኔውን ለማስፈጸም ቢሮው ከጻፈው ደብዳቤ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመመልከት ችሏል።
በጥናቱ መሰረትም አንዳንድ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አደረጃጀቶች ላይ ማሻሻያ መደረጉን አሳውቋል።
° በዚህም መሰረት በክፍለ ከተማ ደረጃ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ታጥፎ በቡድን ደረጃ በዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ስር እንዲደራጅ።
° የስራ አስኪያጅ ፑል እና የዋና ስራ አስፈጻሚ ሦስት አማካሪ መደቦች አደረጃጀታቸው እንዲታጠፍ።
° በወረዳ ደረጃም ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፣ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቅ/ጽቤት ፣ባህልና ኪነጥበብ ጽ/ቤት፣ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት እና ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት እንዲታጠፉና ስራው በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲከናወን።
° የወረዳው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት እና የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት በማዋሃድ በከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት የሚከናወኑ ተግባራት በጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት እንዲከናወኑ እና የ ጽ/ቤቱ ስያሜ " የጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት " በሚል እንዲደራጅ።
° የዋና ስራ አስፈጻሚው አማካሪ አደረጃጀት እንዲታጠፍ ተወስኗል።
ውሳኔው ከሃምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያዝ ሲሆን እንዲታጠፉ ውሳኔ የተላለፈባቸው ጽ/ቤቶች እና አደረጃጀቶች መዘጋት መጀመራቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰራተኞቹ ለማረጋገጥ ችሏል።
እንዲታጠፉ ውሳኔ የተላለፈባቸው ጽ/ቤቶች ተዘግተው ተገልጋዮችም ወደ ክፍለ ከተማ በመሄድ አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተነገራቸው ስለመሆኑ ስሜ አይጠቀስ ካሉ የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ጽ/ቤት ባለሞያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ባለሞያዋ በሌላ ክፍል ድልድል እስኪከናወንላቸው ድረስ ስራ ሳይገቡ በቤት እንዲቀመጡ የተነገራቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም " ከስራ አለመባረራችንን እና የሃምሌ ወር ደሞዝም እንደሚገባልን ተነግሮናል " ያሉ ሲሆን ድልድሉ እስኪከናወን በትዕግስት እንዲጠብቁ እንደተነገራቸው አመልክተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤526😡37🤔27🙏20🕊14😭13👏3😱3😢2💔1
#AddisAbaba
በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ4 ኪሎ ፕላዛን ፣ የ4 ኪሎ የገበያ ማዕከልን እና የመኪና ማቆሚያን በማስመረቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ምን ይዟል ?
- ከመሬት በታች የተገነቡ ዘመናዊ የሆኑ 102 የስጦታ እና የአልባሳት መደብሮች፣ ካፌዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ማንበቢያ ስፍራዎች፣ ሱፐር ማርኬቶች፤
- ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ የመኪና ማቆሚያ፤
- በአንድ ጊዜ እስከ 5,000 ሰዎችን መሰብሰብ የሚያስችል የፕላዛ፣ የአንፊ ቴአትርና የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን ማቅረቢያ ስፍራዎችን ይዟል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ " ፕሮጀክቱ የሲቪል ተሳትፎን፣ የባህል ዕድገትን፣ የእግር ጉዞን የሚያበረታታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ነው " ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን አመልክተዋል።
#MayorOfficeofAA

❤941😡260👏73🙏17🥰16🤔15💔14😢12😱9🕊9