#Sidama
🔴 የሲዳማ ክልል ም/ቤት አቶ ዳዊት ዳንግሳን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾመ።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ምርጫ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላለፉት ሶስት ቀናት በ11 አጀንዳዎች ላይ ሲወያይ ቆይቷል።
በዚህም የ2018 ዓ/ም በጀት፣ የተለያዩ ሹመቶችን እንዲሁም አዳዲስ አዋጆች በማፅደቅ ተጠናቋል።
በጀትን በሚመለከተ ፦
የክልሉን የ2018 ዓ.ም በጀት 32 ቢሊዮን 823 ሚሊዮን 357 ሺህ 21 ብር እንዲሆን አፅድቋል።
ከበጀቱ 19 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን 298 ሽህ 596 ብር ከክልሉ የውስጥ ገቢ የሚሰበሰብ እንደሆነም ተመላክቷል።
ሹመትን በሚመከተ ፦
ምክር ቤቱ በርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደስታ ሌዴሞ የቀረቡ ሹመቶችን ተቀብሎ ያፀደቀ ሲሆን በዚሁ መሰረት :-
➡️ አቶ ዳዊት ዳንግሳ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ (በዚህ ቦታ የነበሩት አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ በወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወሳል)
➡️ አቶ ፍቅሬኢየሱስ አሸናፊ የመሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮኃላፊ
➡️ አቶ ቢንያም ሰለሞን በጠቅላ ፍርድ ቤት የፍርድ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት
➡️ አቶ ገነነ ሹኔ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሹመዋል።
ፍትሕን በሚመለከት ፦
በክልሉ በ2017 በጀት ዓመት በወንጀል እና ፍትሐብሔር መዝገቦች 43 ሺህ 653 አዳዲስ የክስ መዝገቦች የቀረቡ እንዲሁም 1 ሺህ 480 መዝገቦች ከካለፈው ዓመት የዞሩ በድምሩ 45 ሺህ 133 የክስ መዝገቦች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን 44 ሺህ 307 መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውንና ቀሪዎቹ 826 መዝገቦች ለቀጣይ ዓመት መዘዋወራቸዉ በጉባኤዉ ላይ ተገልፆል።
ኦዲትን በሚመለከት ፦
ለምክር ቤቱ በቀረበዉ ልዩ ልዩ የኦዲት ሪፖርቶች በሲዳማ ክልል የበጀት አስተዳደር፣ ውሎ አበል፣ በነዳጅ ክፊያና በፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ጥራት ላይ የታዩ ክፍተቶቾ ለምክር ቤቱ ቀርበዋል።
በምክር ቤቱ ከተነሱ የኦዲት ሪፖርቶች መካከል ፦
° ያለ አግባብ የተከፈለ የአበል ብር 2,567,732,09 /ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሰባት ሺ ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር ከዘጠኝ ሳንቲም/ ፤
° ያላግባብ የተከናወነ የነዳጅ ግዢ ብር 60,940,354,58 /ስልሳ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ አራት ብር ከሃምሳ ስምንት ሳንቲም/ ይገኙበታል።
አዋጆችን በተመለከተ ፦
የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 50/2017 ዓ/ም ፣ የአስፈጻሚ አካላት ማቋቋሚያ፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ የአዋጅ ቁጥር 51/2017 ዓ/ም፤ የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 52/2017 ዓ/ም እና የሀዋሳ ከተማ መዋቅራዊ የዉስጥ አደረጃጀትን መልሶ ለማዋቀር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 53/2017 ዓ/ም ቀርቦ ዉይይት ከተደረገባቸው በኋላ ፀድቀዋል።
የክልሉን ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አደረጃጀት ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን እንዲሁም የክልሉን መንግስት አስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ እና ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የወጡ አዋጆችንም አፅድቋል።
በአዋጁ መሠረት የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተጠሪነቱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆንና በክልል መዋቅር ያሉ 20 ቢሮዎች ሰምና መጠሪያ ማሻሻያ የተደረገባቸዉን ጨምሮ በርዕሰ መስተዳድሩ ሰብሳቢነት የመስተዳድሩ ምክር ቤት አባላት እንደሆኑ አዋጁ ይደነግጋል።
በሌላ በኩል የሀዋሳ ከተማ መዋቅርን መልሶ ለማደረጃት የቀረበዉ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ቀደም የነበረዉን የክፍለ ከተማ ብዛት ስያሜ ላይ ለዉጥ በማድረግ በ5 ክፍለ ከተሞችና በ26 ቀበሌዎች ዳግም እንዲዋቀር በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
ፎቶ፦ የክልሉ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia

❤465🙏18💔13😡10🕊9🥰8👏8🤔7😱7😢2😭1
#Sidama
" ተከራይተዉ በሚኖሩበት ቤት ነዉ ሞተዉ የተገኙት ! " - የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኮሚኒኬሽን
የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሙሉነህ ተክሉ በአለታ ወንዶ ከተማ ተከራይተው በሚኖሩበት ቤት ውስጥ እራሳቸውን አጥፍተው መገኘታቸውን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ቄዲዳ ሻመና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ኃላፊዉ ዛሬ ጠዋት ቢሮ ገብተዉ ባለጉዳይ ጭምር ሲያነጋግሩ እንደነበርና ምሳም ከጓደኞቻቸዉ ጋር በልተዉ ወደ ቤታቸዉ መሄዳቸዉንና ከቀኑ 8 ሰዓት አከባቢ ይህ ጉዳይ መሰማቱንም ገልፀዋል።
ከአማሟታቸዉ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን የገለፁት ኃላፊዉ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ' በግምገማ ምክንያት ነዉ ' የሚሉና ሌሎችም መረጃዎች ከእዉነት የራቁና በቅርቡ የዞና መንግስት ያካሄደዉ ምንም አይነት ግምገማ አለመኖሩን ገልፀዋል።
አቶ ሙሉነህ ተክሉ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ከመሆናቸው በፊት የአለታ ጩኮ ከተማ ከንቲባ ሆነዉ ሲሰሩ መቆየታቸውንና ከስራ ባልደረቦቻቸዉና ከመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ጋር ተግባብተው ሲሰሩ እንደነበር አቶ ቄዲዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኃላፊው አሟሟት ጋር በተያያዘ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያን አዛዥን ለማነጋገር ሞክሮ ጉዳዩ አሁናዊና መረጃ የማደራጀት ስራ ላይ መሆናቸውን በመግለፅ በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታዉቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHwassa

❤588😭560💔42🤔36🕊29😢22🙏17👏8😱8🥰6