TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OFC

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ መጀመሩን የህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤቱ በላከልን መረጃ ገለጸ።

" በአገሪቱ ላይ የተደቀነውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የፀጥታ ቀውስ ለመገምገም እና የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችለውን ወሳኝ ስብሰባ ነው " ብሏል።

ዛሬ ስብሰበው በፓርቲው የውስጥ አቅም ግንባታና ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ላይ ያተኮረ እንደነበር አመልክቷል።

የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲውን አመራርና ድርጅታዊ ብቃት ለማጠናከር ልዩ ሥልጠናዎችን እንደወሰዱና ሥልጠናው በፍጥነት በሚለዋወጥና ፈታኝ በሆነው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የኦፌኮን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረፅ ያለመ እንደሆነ ገልጿል።

ነገ ደግሞ ውይይቱ ትኩረት " በኦሮሞ ሕዝብ፣ በኢትዮጵያና በሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ክልል ላይ በተደቀኑት ከባድ ፈተናዎች ላይ ይሆናል " ብሏል።

" በአጀንዳው ውስጥ በዋናነት የተካተቱት ጉዳዮች በቀጠለው ጦርነትና ማኅበረሰቡን ባወደመው ከፍተኛ የፀጥታ እጦት፣ በመንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የተባባሰው ከባድ የኢኮኖሚ ችግር፣ የተንሰራፋው የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ስር የሰደደው ሥርዓታዊ ሙስና ናቸው " ሲል ገልጿል።

በእነዚህ ውይይቶች ማዕከላዊው ጉዳይ ፓርቲው ለመጪው የ2018 አገራዊ ምርጫ ያለው ስትራቴጂ እንደሆነ አመልክቷል።

" ኦፌኮ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና እምነት የሚጣልበት ምርጫ በማካሄድ እውነተኛ የዲሞክራሲ ሽግግርን ለማረጋገጥ መንግሥት እንደ ቅድመ ሁኔታ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲከፍት ተጨባጭና ሊረጋገጡ የሚችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥያቄዎቹን በይፋ ያቀርባል " ብሏል።

ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኃላ ፓርቲው ይፋዊ መግለጫ እንደሚያወጣ ጽ/ቤቱ በላከልን መረጃ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
557😡94🤔22🙏17👏13🕊12😱11😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OFC

" በሰላማዊ ትግል ለመቀጠል ቁርጠኛ ነኝ " - የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)

🗳" በ2018 ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ቁልፍ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠናል ! "

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን መደበኛ ጉባኤ ዛሬ እንዳጠናቀቀ ገለጸ።

ፓርቲው በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

" ሀገሪቱ የመንታ መንገድ ላይ ትገኛለች " ያለው ፓርቲው " ቀጣዩ ምርጫ 'በዲሞክራሲያዊ መታደስ ወይም በሀገር መፍረስ' መካከል የሚደረግ " ነው ብሏል።

" ያለፉት ሰባት ዓመታት 'የባከነ ተስፋ' የታየባቸው እንዲሁም የፖለቲካ፣ የጸጥታና የኢኮኖሚ ቀውሶች እርስ በርስ እየተመጋገቡ ወደ ከፋ ጥፋት ያመሩበት ጊዜ ነበር " ሲል ገልጿል።

" ለዚህ ሀገራዊ ውድቀት ዋነኛውን ምክንያት በሕብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተፈጸመ ስልታዊ ጥቃትና ሰላማዊ የፖለቲካ አማራጮች በሙሉ መዘጋታቸው ነው " ሲል አመልክቷል።

ፓርቲ በመጪው የ2018 ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው በቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ገልጿል።

ኦፌኮ " 'ለተሰባበረ የፖለቲካ ሂደት' ሕጋዊ ዕውቅና አልሰጥም " ያለ ሲሆን " በምርጫው ፍተሃዊነትና ታዓማኒነት የሚረጋገጠው መንግሥት መሰረታዊ የሆነ ዳግም ማስተካከያ ሲያደርግ ብቻ  ነው " ብሏል።

ፓርቲው " ቁልፍ " ያላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ይፋ አድርጓል።

" እነዚህም ፦

1. በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው ጦርነት በአፋጣኝና በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተረጋገጠ መልኩ እንዲቆም እና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር።

2. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤ ይህም ለሀገራዊ እርቅ መሰረት እንዲሆን። የፖለቲካ ነጻነቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ፤ የታሸጉ የኦፌኮ ቢሮዎች እንዲከፈቱ እንዲሁም አፋኝ የሆኑ፣ የምርጫ ፣የሚዲያና የሲቪል ማህበረሰብ ሕጎች እንዲሻሩ።

3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብን አመኔታ መልሶ እንዲያገኝ በሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር። " የሚሉ ናቸው።

ኦፌኮ በማጠቃለያው " የኦሮሞ ህዝብ አንድነቱን እንዲያጠናክር " ሲል ጥሪ አቅርቦ " ከሌሎች የኦሮሞና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ቃልኪዳን ለዲሞክራሲ ለመፍጠር የትብብር እጁን መዘርጋቱን " አመልክቷል።

"  ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በመንግሥት ላይ ተጨባጭ ጫና ያሳድር " ሲል ገልጿል።

ኦፌኮ ፥ በሰላማዊ ትግል ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቆ " ለዲሞክራሲ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ዋነኛው ኃላፊነት በገዥው ፓርቲ ላይ የሚወድቅ ነው " ሲል አቅጣጫ አስቀምጧል።

መረጃውን የላከው የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ነው።

#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
665😡117🤔29🕊26👏12🙏5😭4😱2