TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 " አሁን የ2,000 ብር ደሞዝ የለም በሌለ ነገር ከዚያ በታች ያለው ነጻ ነው ብንል ታክስ መቀነስ አይደለም ! " - የምክር ቤት አባል በገቢ ግብር ማሻሽያ አዋጅ ላይ ዝቅተኛ  የግብር ከፋይ መነሻ ደመወዝ 5,000 ብር እንዲሆን በምክር ቤት ተጠየቀ፡፡ ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ  ከሰዓት በጠራው ልዩ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ አሁን በስራ ላይ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የኑሮ ውድነትን ታሳቢ በማድረግ የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ከ2,000 ብር ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጠንካራ ጥያቄ ቀርቧል።

ጥያቄው የቀረበው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በፓርላማው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገዉ ዉይይት ላይ ነው።

በአሁኑ ረቂቅ አዋጅ መሰረት፣ ከ2,000 ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር እንዲከፈል የሚለው ሀሳብ ቀርቧል።

ይህ የገቢ ግብር አዋጅ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ስራ ላይ መዋሉ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን በማሻሻያው ከግብር ነፃ የሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ በ300% በማሳደግ ወደ 2,000 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

በተጨማሪም፣ ከፍተኛው የማስከፈያ መጣኔ የሆነው 35% ግብር የሚያርፍበት ገቢ ደግሞ ወደ 14,000 ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፣ የአዋጁ መሻሻል መንግስት ግብር በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚረዳ ገልጸዋል።

ከግብር ከፋዩ ህብረተሰብ የሚነሱ " ግብር በዝቷል ይቀነስ " የሚሉ ሀሳቦች ሚዛናዊ በሆነ መልኩ እንደሚታዩም አክለዋል።

በውይይት መድረኩ ከተነሱት አስተያየቶች መካከል፣፦
- የገቢ ግብር መነሻው ከአምስት ሺህ ብር ጀምሮ እንዲሆን፣
- ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መልኩ ግብር እንዲቀነስ፣
- በተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንፃር በደንብ እንዲታይ የሚሉ ሀሳቦች ቀርበዋል።

የመረጃው ባለቤት የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
989👏120😭84😡80🕊32🙏24😢11🤔10🥰4😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ዛሬ ወሬ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የሃይማኖት አባቶች ልዑክ በመቐለ ! ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጥዋቱ ትግራይ ክልል መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የደረሰው የሃይማኖት አባቶች ልዑክ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የተወጣጣ ሲሆን አጠቃላይ ልዑኩ ከ20 በላይ አባላት አሉት። የሰላም ልኡኩ ከአውሮፕላን ማረፍያ በቀጥታ ወደ መቐለ ፕላኔት ሆቴል አዳራሽ በማመራት በፕሬዜዳንት…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ " በአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚደረግ ምክክርና እርቀ ሰላም ፍሬው ጣፋጭ ነው " አሉ።

ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ዛሬ ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መክረዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ስለተካሄደው የሰላም ውይይት አስመልከተው በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው በትግርኛ ባጋሩት መረጃ " የኢፌዲሪ መንግስት በሽምግልና እና ምክክር ችግሮች እንዲፈቱ ቅድምያ ሰጥቶ እንደሚሰራ በተለያዩ ጊዚያት በተግባር አሳይቷል " ብለዋል። 

" በረጅሙ የአገሪቱ የአገረ መንግስት ስርዓት አገራዊ እርቅ ፣ አገራዊ ምክክር ፣ ፓለቲካዊ ውይይት የሚሉ ማህበራዊ አምዶች በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውይይት በይፋ እንዲተገበሩ ያደረገው የአሁኑ መንግስት መሆኑ መካድ የለበትም " ብለዋል።
  
" ግጭት ሌላ ግጭት እየወለደ በችግር አዙሪት ከመኖር ያለፈ ሌላ ፋይዳ የለውም " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ " በውይይትና መግባባት ችግሮቻችን በመፍታት ሰላምን በፅኑ መሰረት እናኑር " ብለዋል። 

" ከተለያዩ የትግራይ የማህበረሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አካላት ለቀጣይ መደረክ ምቹ መደላድል የሚፈጥር ውይይት አካሂደናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተካሄደው ጥልቅ ውይይት በጥያቄና መልስ የታጀቡ በርካታ ጉዳዮች እንደተነሱ ገልጸዋል።

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ያሉት ተግዳሮቶች እንዴት መታረም አለባቸው ፣ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮች መቆምና መታረም እንዳለባቸው በተለይ የተፈናቃዮችና ትግራይን መልሶ መገንባት ጉዳይ የምክክሩ ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ ብለዋል።

የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በአገሪቱ ፓለቲካና ኢኮኖሚ በብርቱ ተዋናይ የሚሆኑበት ሁኔታ መፍጠር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነና ሌሎች ጉዳዮች ተነስው መግባባት ተደርሶባቸዋል ብለዋል።

" የፌደራል መንግስት ከህዝብ ፣ ከጊዚያዊ አስተዳደሩና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በፓለቲካ በፀጥታና ኢኮኖሚ እንዲሁም በትግራይ መልሶ ግንባታ ዙሪያ ተቀራርበን እንደምንሰራ ደገመን እረጋግጠንላችኋለን " ብለዋል።

የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም በመቐለ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከተወያዩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ነው ዛሬ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር ) ጋር ውይይት ያደረጉት ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

ፎቶ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
946😡325🕊101🤔32🙏30😭17🥰10💔9😢4😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ምንድነው ያሉት ? 🔴 ፕሬዝዳንቱ አብዛኛው ንግግራቸው ስለ ሀገራቸው ኤርትራ የውስጥ ጉዳይ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ሀገራት ጉዳይ ነበር ! ኤርትራ ትላንት ቅዳሜ 34ኛ ዓመት የነፃነት በዓሏን አክብራለች። ለ34 ዓመታት አገሪቷን በብቸኝነት እያስተዳደሩ ያሉት ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለ34ኛ ጊዜ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዜዳንቱ 20 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው ንግግራቸው…
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ስለ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ምን እያሉ ነው ?

ከሀገራቸው ጉዳይ ይልቅ ስለ ሰው ሀገር ጉዳዮች ሰፊ ጊዜ ወስደው በመናገርና በመተንተን የሚታወቁት የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ምሽት በሀገራቸው ብቸኛው ቴሌቪዥን በተላለፈ ቃለ መጠይቅ #የኢትዮጵያን ስም ደጋግመው ሲያነሱ ታይተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከወራት በፊት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ከሀገራቸው ጉዳይ ይልቅ ስለ ኢትዮጵያ እና ቀጠናው ጉዳይ ትንታኔ ሲሰጡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። በወቅቱም ኢትዮጵያ ስሟን እያነሱ ለተናገሩት ነገር ሁሉ በቀጥታ አንዳችም ምላሽ ሳትሰጣቸው በዝምታ አልፋቸዋለች።

ትላንት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ደግሞ ንዴትን በቀላቀለ ሁኔታ በማይመጥኑ ቃላት የኢትዮጵያን ስም ሲያነሱ ነበር።

በተለይም ኢትዮጵያ ያነሳችውን የባህር በር ጥያቄ ሲያጣጥሉት ነው ያመሹት።

የኢትዮጵያን የወደብ እና የባህር በር ጥያቄ " የህጻን ጨዋታ ነው፣ ማሳሳቻ ነው፣ የረከሰ ውሸት ነው ፣ የውስጥ ጉዳይ ማዳፈኛ ነው ፣ ጀርባው የተባበሩት አረብ ኤሜራት የወደብ ማስፋፋት አጀንዳ ነው " የሚሉ ቃላቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማጣጣል ሞክረዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በርን ጉዳይ አለም አቀፍ አጀንዳ ማድረጓን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ለጥያቄዋ ድጋፍ ማድረጋቸውም ፕሬዝዳንቱን እንዳላስደሰተ የሚጠቁም ንግግርም ሲናገሩ ነበር።

" ፈረንሳይ ከኛ ጋር ናት፣ አሜሪካ ፣ ኤማራት፣ አውሮፓ ህብረት ከኛ ጎን ናቸው ማለት ጭንቅ እንጂ የድል መንገድ አይደለም " በማለት " ኢትዮጵያውያን የውስጥ ችግራችሁን ፍቱ " ሲሉ ተደምጠዋል።

በኢትዮጵያ በኩል ሀገራቸው ላይ የጦርነት  ስጋትና ዛቻ እንዳለ በማመላከትም " እራሳችንን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ለባሕር ስትል ኤርትራንም ሆነ የትኛውንም ጎረቤት ሀገር የመውጋት አንዳችም ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ ማሳወቋ ይታወሳል። ነገር ግን የባህር በር ጉዳይ ህልውናዋ መሆኑን ለዓለም ህዝብ አስረግጣ ተናግራለች።

ሌላው ፕሬዜዳንቱ ኢትዮጵያ ተመድ ሄዳ ከሳናለች (ክሱ ፦ ድንበር አካባቢ አሁንም የኤርትራ ጦር ግፍ እየፈጸመ ስለመሆኑ)  " ያሉም ሲሆን " ክሱ አስነዋሪና አሳፋሪ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነትም ሲያነሱ ነበር።

ገና የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሲፈረም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንዳሻከረች በይፋ የሚታወቅ ቢሆንም " ኤርትራን ከመክሰሳችሁ በፊት የፕሪቶሪያን ውል ተግብሩ ፤ የውስጥ ችግራችሁን መፍታት አስቀድሙ ፤ ለምን ስምምነቱ በቅን ልቦና አልተተገበርም ለምን ፋኖ ላይ ጦርነት ከፈታችሁ ? " የሚል ንግግርም ተናግረዋል።

ሌላው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሌለባት ፣ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የማይታወቅባት ኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን በተመለከተ ንግግራቸው " በኢትዮጵያ መታየት ጀምሮ የነበረው የለውጥ ተስፋ ጨልሟል ፤ የፖለቲካ ፓርቲ ብሎ የለም " የሚል ንግግር አሰምተዋል።

ያለአንዳች ተቀናቃኝ ከ30 ዓመት በላይ  ኤርትራን እየገዙ ያሉት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደ ሁል ጊዜው የትላንት ምሽቱ ቃለ ምልልሳቸው ስለ ሀገራቸው ጉዳይ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እንዲሁም ስለ ሌሎች ሀገራት ጉዳይ በመተንተን ነው ያለፈው።

ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲወርድ ከተደረገ በኃላ የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እስኪፈረም ድረስ ኢትዮጵያን እና አስተዳደሯን ሲያሞካሹ እንደቆዩ በአደባባይ የሚታወቅ ሀቅ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.41K😡176🕊73🤔48👏40🙏16🥰10😭9😢7💔6😱4